• +251462204629
  • Hawassa , Ethiopia

ቢሮ ኃላፊ መልዕክት

የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል መንግስት ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ

    የአቶ ተፈሪ አባተ መልዕክት
እንኳን ወደ ደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል መንግስት ፋይናንስ ቢሮ ድረገፅ በሰላም መጣችሁ፡፡
ቢሮው የክልሉን የፊስካል ፖሊሲ አተገባበር ማዕቀፍ ማዘጋጀትና መተግብር፣ የክልሉን መንግስት በጀት ማዘጋጀትና ማስተዳደር፣ በተፈቀደው በጀት መሠረት ክፍያ መፈጸም፣ የበጀቱን አፈጻጸም መከታተል፤ የክልሉ መንግስት የበጀት፣ የሂሳብ፣ የክፍያና ጥሬ ገንዘብ እና የውስጥ ኦዲት ሥርዓት መዘርጋትና በስራ ላይ እንዲውል ማድረግ፣ የክልሉን መንግስት የገንዘብ ሰነዶች፣ ገንዘብና ንብረቶች መያዝና ማስተዳደር፣የክልሉ መንግስት የብድርና እርዳታ ስምምነቶችን መፈራረምና ከአጋር ድርጅቶች የሚገኘውን ሀብት ውጤታማና በተቀላጠፈ አኳኋን ማስተዳደርና አፈጻጸሙን መከታተል፣ የክልሉን መንግስት የፋይናንስና ንብረት ኢንስፔክሽን ማከናወን፣ ዘመናዊ የበጀት አስተዳደር፤ የሂሳብ አያያዝ፣ የግዥና የንብረት አስተዳደር፣ በኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት ዘርፍ የተሰማሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ማስተባበርና መቆጣጠር፤ ለሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች የቅድመ ስምሪት የስራ ውል ፈቃድ መስጠት፣ አተገባበራቸውንም በመስክ የመከታታልና የመገምገም እንዲሁም የሀብት ፍሰትና ስርጭት ፍትሃዊነት እንዲረጋገጥ ማስቻል፣ በክልሉ የሚገኙ የመንግስት ልማት ድርጅቶችን እንቅስቃሴ ትርፋማነታቸውንና የገበያ ትስስራቸውን መከታተል፣ መቆጣጠርና አፈጻጸሞችንም በመገምገም ግብረ-መልስ መስጠትና ማስተካከያዎችን ማድረግ፣ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣንና ተግባር መሠረት በበላይነት የመምራት ዋና ኃላፊነት አለበት፡፡
በመንግስት የተነደፈ የልማት ፕሮግራሞች ለማሳካትና ድህነትን ለመቀነስ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ የሚቻለው የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር ውጤታማ ሲሆን ነው፡፡ ይኸውም ውጤታማ የሆነ የፕሮግራም በጀት መተግበር፣ ዘመናዊ የጥሬ ገንዘብ ክፍያ መዘርጋት፣ ዘመናዊ የመንግስት የሂሳብ አያያዝና የሪፖርት አቀራረብ መተግበር፣ የመንግስትን ገንዘብ ከብክነት ለመከላከል የሚያስችል ጠንካራ የውስጥ እና የውጭ ኦዲት ማቋቋምና መተግበር፣ የፋይናንስ ሥራውን የሚደግፍ ዘመናዊ የመረጃ ሥርዓት መዘርጋት፡፡ የክልል ፊስካል ፖሊሲም የብልፅግና ጉዞ ዓላማዎችን ለማስፈፀም በመንግስት ገቢ፣ ወጪ፣ ብድርና የውጭ እርዳታ አስተዳደር አማካኝነት ሥራ ላይ የሚውል ሌላው ቁልፍ መሣርያ ነው፡፡ በመሆኑምየመንግስትን ሀብት በብቃት ለማስተዳደር አቅም ያለው ጠንካራ እና ውጤታማ ተቋም ለመሆን እንጥራለን፡፡
በሀገራችን የተጀመረዉን ፍኖተ ብልፅግና ጉዞ በማፋጠን በ2012 የኢትዮጵያ የነፍስ ወከፍ ገቢ 953.18 ዶላር ከነበረበት በ2022 ወደ 2,220 ዶላር ለማድረስ የተያዘውን ግብ በክልላችን ለማሳካት በሚደረገዉ ርብርብ ወሳኙን ምዕራፍ የያዘ ሲሆን፣ በክልላችን በብልፅግና ጉዞ የዜጎችን ቁሳዊ ፍላጎት፣ ዕኩል የልማት ተሳታፊነት፣ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እና ነፃነትን ለማረጋገጥ የክልሉን ሀብት በብቃት በማሰተዳደርና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ልማት በማረጋገጥ መሰረታዊ የኢኮኖሚ ለውጥ መጥቶ ይህ ራዕይ እውን የማድረግ ጉዞ ረጅምና ፈታኝ ቢሆንም የተቀመጡትን ግቦች ለማሳካት እንቅፋት የሆነብንን የፋይናንስ እና የሰለጠነ የሰው ኃይል በተላይ የሴቶችን ተዋፆ ያለገናዘበ የለውን ችግር ለመቅረፍ ከልማት አጋሮች የሚገኝ እርዳታ አንዱ አማራጭ ነው፡፡ ሀገሪቱ ቅድሚያ በምትሰጣቸው ዘርፎች እንደ ግብርና፣ ውሃ፣ ትምህርት፣ ጤና፣ ኢነርጂ፣ መሠረተ ልማት የመሳሰሉትን በብቃት ለመተግበር ከውጭ ትብብር የሚገኙ ድጋፎች ጠቃሚነታቸው የጎላ ነው፡፡ በመሆኑም በትብብር የተገኘ ሀብትን በአግባቡ ለታለመለት ግብ በማዋል ራዕያችንን ማሳካት ከእያንዳንዱ ባለ ድርሻ አካል የሚጠበቅ ግዴታ ነው፡፡
ኢኮኖሚያዊ ስኬቶቻችን እውን ሊሆኑ የቻሉትም በመንግስትና በህዝብ የጠነከረ ግንኙነት ሲኖር በክልሉ በመንግሰት መ/ቤቶች የሚመደበዉን ሀብት በተገቢው ለፀደቀዉ ዓላማ ብቻ በሥራ ላይ እንዲዉል የሚደረግ ሲሆን የሀብት አጠቃቀሙም በቁጠባ፣ በብቃትን እና ዉጤታማነትን በከፍተኛ ደራጀ ሊያሰገኝ በሚችል መንገድ መፈጸሙን የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት በሁሉም መስክ ባሳተፈ መልኩ ድጋፋዊ ክትትል እና ግምገማ ስርዓት በመዘርጋት በሚገኙ ክፍተቶች ላይ የማስተካከያ እርምጃ እየተወሰደ የሚመደበው ሀብት ለአለማው እንዲዉል በማድረግ በሚገኘዉ ዕድገት የዜጎችን ዕኩል ተጠቃሚነት የሚረጋግጥ ይሆናል፡፡
                                                               ክቡር አቶ ተፈሪ አባተ
                                                              የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ