• +251462204629
  • Hawassa , Ethiopia

የሥርዓተ ጾታንና የሕፃናትን ጉዳይ በልማት ማካተትና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ በሚመለከት አመራሩ ትኩረት አልሰጠውም ተባለ

Welco

ከኮሮና በሽታ መከሰት በኋላ ጾታዊ ጥቃትና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች መጨመራቸው ተገለጸበደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት በፋይናንስ ሴክተር የሥርዓተ ጾታንና የሕፃናትን ጉዳይ በልማት ማካተትና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ በሚመለከት አመራሩ ትኩረት እንዳልሰጠው ተገለጸ፡፡ ይህ የተገለጸው ሰሞኑን በዞን ደረጃ ለሚገኙ ለሥርዓተ ጾታና የሕፃናትን ጉዳይ በልማት ማካተትና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ባለሙያዎች ሥልጠና በተሰጠበት ወቅት ነው፡፡ አቶ ዘርፉ አጥናፉ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ ሥልጠናው ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት የሕዝቡን ሃምሣ በመቶ በላይ የሆኑት ሴቶችን በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማኅበራዊ ዘርፍ ሳናሳትፍ ዕድገት ማምጣት አንችልም ብለዋል፡፡ ስለሆነም በየዞኑ የሚገኙ ባለሙያዎች በየተመደቡበት የሙያ ዘርፍ የሥርዓተ ጾታና የሕፃናትን ጉዳይ በልማት ማካተትና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥን በሚመለከት በትጋት እንዲሠሩና አመራሩም አስፈላጊውን ትኩረት መስጠት ይኖርበታል ሲሉ አሳስበዋል፡፡ይህንን አስመልክቶ በቢሮው የሥርዓተ ጾታና የሕፃናትን ጉዳይ በልማት ማካተትና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ፀሐይ ገነቱ ባቀረቡት የመነሻ ጽሑፍ በዝርዝር እንደታየው አብዛኛዎቹ የዞኖች መምሪያዎች የሥርዓተ ጾታን ጉዳይ በመምሪያው ዕቅድ ውስጥ አያካትቱም፣ ሪፖርትም አያዘጋጁም፣ መረጃም አያደራጁም፣ እንዲሁም ለወረዳዎች ድጋፍና ክትትል አላደርጉም ተብሏል፡፡ ከጉራጌ፣ ከምባታ ጠምባሮ፣ ወላይታ፣ ጋሞና ሀዲያ ዞኖች በስተቀር ሌሎቹ ማለትም ጎፋ፣ ስልጤ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ከፋ፣ ሸካ፣ ዳውሮ፣ ኮንሶ፣ ሀላባና ደቡብ ኦሞ ዞኖች ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ያላሳዩ መሆናቸው ተገልጿል፡፡በአንፃሩ ጉራጌና ከምባታ ጠምባሮ ዞኖች የተሻለ እንቅስቃሴ ያሳዩ ሲሆን፣ ዕቅድን በማዘጋጀት፣ ወቅታዊ ሪፖርቶችን ተደራሽ በማድረግ፣ በጾታ የተለየ የተጠቃሚነት መረጃ በማሰባሰብ፣ የየመምሪያዎቻቸውን ዕቅድ በመፈተሽ፣ የሕፃናት ማቆያዎችን በማቋቋም፣ ለድሃ ድሃ ሴቶችና ሕፃናት ዕርዳታ በማሰባሰብ፣ ለወረዳዎች ድጋፍና ክትትል በማድረግ፣ የደም ልገሳን በማስተባበር እና በሌሎች እንቅስቃሴዎች ጉልህ እንቅስቃሴ ማድረጋቸው በተሞክሮነት ቀርበዋል፡፡ ከውይይቱ ለመረዳት እንደተቻለው አበራታች የአመራሩ ድጋፍ በተገኘበት ጥሩ ውጤት የተመዘገበ ሲሆን የአመራሩ ደጋፍ በሌለበት ምንም ውጤት አልተመዘገበም ተብሏል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ጾታዊ ጥቃትና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ከኮሮና በሽታ መከሰት በኋላ መጠናቸው መጨመሩ በዚሁ መድረክ ላይ በቀረበ አንድ ጥናት ተገለጸ፡፡ በዚሁ መሠረት በሴቶችና ሕፃናት ላይ ድብደባ መፈጸም፣ ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር፣ ያለዕድሜ ጋብቻና የሴት ልጅ ግርዛት፣ በጋብቻ ላይ ጋብቻ፣ ጠለፋና የቀለብ ክልከላ በዋናነት ተጠቅሰዋል፡፡በሴቶችና ሕፃናት ላይ እየደረሰ ያለውን ችግር ለመፍታት እንደ ተግዳሮት ከተጠቀሱት ውስጥ በፍ/ቤቶች ወጥ የሆነ፣ አገልግሎት አለመሰጠቱ፣ የማረሚያ ተቋማት የቅበላ መጠን ማነስ፣ በክልል የሚገኙ የመርማሪ ፖሊሶች ቁጥር ማነስና የአቅም ውስንነት መኖር፣ የልዩ ይቅርታ ተጠቃሚዎች በህብረተሰብ እና በፍትህ ተቋማት ላይ ጫና ማሳደራቸው፣ በጤና ተቋም የጥቃት ሰለባ ለሆኑ ሴቶችና ህጻናት ተገቢውን ፍትህ እንዲያገኙ ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ ከመስጠት አንፃር ክፍተት መኖሩ እና የህክምና አገልግሎትም እንደሌሎች ታካሚዎች ካርድ አውጥተው ክፍያ ፈጽመው መታከማቸው የጤና ሴክተር ጉዳዩን የራሱ እንዳላደረገው ለማየት ተችሏል የሚል ሃሳብ በጥናቱ ተካቷል፡፡

me to WordPress. This is your first post. Edit or delete it, then start writing!

0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *