• +251462204629
  • Hawassa , Ethiopia

ፋይናንስ ቢሮ ለወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ የተገዛውን አውቶቡስ አስረከበ

በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት የፋይናንስ ቢሮ ለወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ የተገዛውን አውቶቡስ አስረከበ፡፡የተገዛውን አውቶቡስ ለእግርኳስ ክለቡ ያስረከቡት አቶ ተፈሪ አባተ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ናቸው፡፡ ኃላፊው አውቶቡሱን ለክለቡ ተወካዮች ካስረከቡ በኋላ ለብዙሃን መገናኛ በሰጡት ቃለመጠይቅ የክልሉ መንግሥት በክልሉ ለሚገኙ የእግር ኳስ ክለቦች ድጋፍ ሲያደርግ ወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ስድስተኛው መሆኑን አስታውሰው፣ መንግሥት ክለቦች ብቁና ጤናማ ዜጋ ለማፍራት የሚያደርጉትን ጥረት ለማድረግ ድጋፉ እንደሚቀጥል እምነቴ ነው ብለዋል፡፡ በዚህም መሠረት ክለቡ ተበረታቶ የድርሻውን ኃላፊነት እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡አቶ እንዳለ ገ/መስቀል የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ በበኩላቸው ክልሉ ያደረገላቸው የአውቶቡስና የገንዘብ ደጋፍ የሞራል ስንቅ እንደሚሆናቸው ገልጸው፣ ክለቡን ውጤታማ ለማድረግ በክልሉና በከተማው አስተዳደር በኩል የሚደረገው ድጋፍ እንደተጠበቀ ሆኖ በቴክኒክ የተሻለ አቅም እንዲኖረው በመሥራት ክልሉን የሚያስጠራ ክለብ እንደሚሆን እምነት አለኝ በማለት ለተደረገው ድጋፍ የክልሉን መንግሥት አመስግነዋል፡፡

0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *