ደረሰኞችና ልዩ ልዩ ሕትመቶች በበቂ ሁኔታ መታተማቸው ተገለፀ
በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኞችና ሌሎች ተዛማጅ ሕትመቶች በበቂ ሁኔታ መታተማቸውን በፋይናንስ ቢሮ የጋራ ግዥና ንብረት ማስወገድ ዳይሬክቶሬት ገለጸ፡፡
አቶ ዓለማየሁ ሀንዳሞ በቢሮ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ለቢሮው ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ባለሙያ እንዳብራሩት በአሁኑ ወቅት ከቀበሌ እስከ ክልል ባሉ መንግስታዊ መስሪያ ቤቶች በቂ የሕትመት ሥርጭት መኖሩን ያረጋገጡ ሲሆን ሕትመትን በወቅቱ በማንሳት ስልጤ፣ ወላይታ እና ጋሞ ዞኖች ግንባር ቀድም ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል፡፡
ይሁን እንጂ የተወሰኑ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ያሳተሙበትን የሕትመት ዋጋ ባለመክፈል የዕዳ ክምችት ያለባቸው ሲሆን ከመቶ ሺዎች እስከ 12 ሚሊዮን ብር ዕዳ ያለባቸው ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች በሥራው ላይ ጫና ፈጥረዋል በማለት አስረድተዋል፡፡
ዕዳው በመንግስት ፋይንንስ በኩል በወጪ መርጃ የሚቀነስበት ሁኔታ ቢኖርም ለዕዳው ማቅለያ በቂ በጀት ባለመመደብ ችግሩን ለማቃለል የሚደረገውን ጥረት አዳጋች አድርጎታል ሲሉ ገልፀዋል፡፡
0