የፋይናንስ ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች ምስጋና ተቸራቸው
ምስጋናዉን ያቀረቡት በደቡብ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ፅሕፈት ኃላፊ የሆኑት አቶ ዘርፉ አጥናፉ ሲሆኑ ወቅታዊውን የሰሜን አዝ ጥቃትና ለመከላከያ ሰራዊቱ ድጋፍ አሰባሰብን በተመለከተ ለቢሮው ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡አቶ ዘርፉ በመግለጫቸው የመከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ አባል የሆኑት ውድ የኢትዮጵያ ልጆች ባለፉት 21 ዓመታት ከጭቁኑ የትግራይ ህዝብ ጋር ሆነው በርካታ የልማት ስራዎችን በመስራት የልማት አጋርነታቸውንና አለኝታነታቸውን ያስመሰከሩ ነበሩ ብለዋል፡፡ አቶ ዘርፉ ንግግራቸውን በመቀጠል ሰራዊቱ የትምህርት ተደራሽነት በሌለባቸው የትግራይ ቦታዎች ከጥቂቷ ደሞዛቸው ቀንሰው ትምህርት ቤት እየገነቡ የትምህርት እድል ያላገኙ እፃናትን የረዱ፣ የጤና ተቋም በሌለባቸው ቦታዎች ጭምር በገንዘብም ሆነ በጉልበት እየተሳተፉ በርካታ ጤና ጣቢያዎችን እና ጤና ኬላዎችን በመስራት ለአካባቢው ማህበረሰብ ያስረከቡ፣ አካባቢው በአንበጣ መንጋ በተወረረ ጊዜ ለአርሶ አደሩ ከፍተኛ እርዳታ ያደረጉ ናቸው፡፡ መከላከያ ሰራዊታችን እንኳን በሃገር ውስጥ በተለያዩ ሃገራት ሰላም በማስከበር ስራው ከፍተኛ ምስጋናና አክብሮት የሚቸረው እንደሆነ የሚታወቅና የተመሰከረ ነው፡፡ ይህንን በተመለከት የደቡብ ክልል ፋይናንስ ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች እነዚህ የእናት ጡት ነካሽ ሆኑ ዘራፊ የህወሃት ቡድኖች በሰሜን እዝ ላይ ያደረሱትን ታሪክ የማይረሳው የክህደት ክህደት የሆነውን ጭካኔ የተሞላበት ጭፍጨፋ በማውገዝና ለድጋፍም በተጠሩ ወቅት ባጠረ ጊዜ ውይይት በማድረግ መከላከያ ሰራዊታችን እየወሰደ ያለዉን ህግ የማስከበርና ሀገር የማዳን ስራ እያከናወኑ ያሉ በመሆናቸው ከእነርሱ ጎን እንቆማለን ያሉ ሲሆን መከላከያ ሰራዊታችን የአካልም ሆነ የህይወት መስዋዕትነት እየከፈለ ያለ ሲሆን አብረን እንዘምታለን፣ ደም እንለግሳለን፣ በማለት ባለፈው ሰኞ ህዳር 7/2012 ባካሄዱት ውይይት ከደሞዛቸው ከ50 እስከ 100 በመቶ ለመስጠት ቃል ገብተዋል በዚህም መሰረት ከ203 ሰራተኞች ብር 691,888.14 /ስድስት መቶ ዘጠና አንድ ሺህ ስምንት መቶ ሰማንያ ስምንት ከ14 ሳንቲም/ በሃገር መከላከያ ሰራዊት የድጋፍ አካውንት ላይ ገቢ ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም በርካታ የሆኑ የቢሯችን ሰራተኞች ደም ለግሰዋል፡፡ ሰራተኞቹ ለመከላከያ ሰራዊታችን የምናደርገውን ድጋፍ የወያኔ ጁንታ ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር እስኪውሉ ድረስ አጠናክረን እንቀጥላለን ማለታቸውን በመግለፅ በመጨረሻም የቢሮው አመራሮችና ሰራተኞች ግፈኛው የወያኔ ዘራፊ ቡድን ግብዓተ መሬቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ ምንም ዓይነት የድርድር ሃሳብ እንዳይቀበል መንግስትን ማሳሰባቸውን በመግለፅ እንዲሁም የቢሮው ጽሕፈት ቤት ኃላፊም ሰራተኞ ላደረጉት አስተዋፅኦ በመከላከያ ሰራዊትና በቢሮው ስም በማመስገን መግለጫቸውን አጠናቀዋል፡፡