- የክልሉን መንግስት በጀት ማዘጋጀት፣ በተፈቀደው በጀት መሠረት ክፍያ መፈጸም፣ የበጀቱን አፈጻጸም ማስተዳደር፣ መገምገምና መቆጣጠር፤
- የክልሉ መንግስት የበጀት፣የሂሳብ፣የክፍያና የውስጥ ኦዲት ሥራዓት መዘርጋትና በስራ ላይ እንዲውል ማድረግና መከታተል፤
- የክልሉን መንግስት የገንዘብ ሰነዶች፣ ገንዘቦችና ንብረቶች መያዝና ማስተዳደር ይገኙበታል፡፡
- የክልሉ መንግስት የብድርና እርዳታ ስምምነቶችን መፈራረምና ማስተዳደር፤
- በኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት ዘርፍ የተሰማሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ስራ ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ማስተባበርና መቆጣጠር፤
- የሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች የብቃት ምዘና ማድረግ፣ የስራ ውል መፈራረም፣ ማስተባበር፣ መከታታልና መገምገም ሥራዎች ይገኙበታል፡
- ዘመናዊ የበጀት አስተዳደር የሂሳብ አያያዝ፣ የግዥና የንብረት አስተዳደር ስርዓት መመስረት፣በስራ ላይ መዋሉን መከታተልና መቆጣጠር፤
- የክልሉን መንግስት የፋይናንስና ንብረት ኢንስፔክሽን ማከናወን፣ እርምጃ መውሰድና እንድወስድ ማድረግ፤
- የክልሉን መንግስት የገቢ ደረስኝ ማሳተም፣ ማሰራጨት፣መከታተልና መቆጣጠር
- በክልሉ የሚገኙ የመንግስት ልማት ድርጅቶችን እንቅስቃሴና ተግባራት መከታተል፣ መቆጣጠርና አፈጻጸሞችን መገምገም
- ዓላማውን ለመፈጸም የሚረዱ ሌሎች ሥራዎችን ማከናወን ተግባራቶች ናቸው፡፡