• +251462204629
 • Hawassa , Ethiopia

የፊስክል ፖሊስና ገቢ ማበልጸግ ዳይሬክቶሬት

 • የመንግስት በጀት በመካከለኛ ጊዜ ዕይታ እንዲመራ የሚያስችልና ለዓመታዊ በጀት ዝግጅት መነሻ የሚያገለግል የመካከለኛ ዘመን የፊስካልና ወጪ ማዕቀፍን ያዘጋጃል፤ ያስተባብራል፣ ማዕቀፉ በክልል ምክር ቤት ፀድቆ ሥራ ላይ ሲውል አፈፃፀሙን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ሪፖርት ያዘጋጃል፣
 • የክልሉ ምክር ቤት በሚወስነው የክልሉ ሀብት ክፍፍል ቀመር መሠረት ፕላን ኮሚሽን ያዘጋጀውን የክልል ማዕከል፣ የዞኖችና ልዩ ወረዳዎች በጀት ድጋፍ (Block Grant) ድርሻ ያዘጋጃል፤ በክልሉ መንግስት ዓመታዊ ረቂቅ በጀት ውስጥ እንዲካተት ያደርጋል፤
 •  የፊሲካል ፖሊሲ ትንተና፣ የበጀት፣ የታክስ ፖሊሲና የብድር አስተዳደር ስራዎችን ያከናውናል፤
 • የሦስት ዓመት ጠቋሚ የመንግሥት ገቢና ወጪ በምንጭ በመተንተን ለይቶ በማዘጋጀት የቀጣይ አምስት አመቱን የመንግሥት ገቢና ወጪ ትንበያ ያካሂዳል፤
 • የአስተዳደር እርከኖችን ጠቋሚ የበጀት ጣሪያ በካፒታልና መደበኛ በጀት ድርሻ ለይቶ ያዘጋጃል፤ በክልሉ መንግስት እንዲፀድቅ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፤
 • የመንግስት ወጪ ፕሮግራም(መወፕ) እና የመንግሰት ኢንቨስትመንት ፕሮግራም(መኢፕ) ዶኩመንቶችን ከዞንና ከክልል ሴክተር መ/ቤቶች ያሰባስባል፤ ያጠቃልላለ፤ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፤
 • ለዓመታዊ በጀት ዝግጅት የሚያስፈልጉ የፖሊሲ መነሻ በማድረግና የተገልጋዮችንና ባለድርሻ አካላትን ችግሮችና ፍላጎቶች ይለያል፤
 • የክልሉን የልማት ግቦች ለማረጋገጥ የሚያስችል የመካከለኛና አጭር ዘመን ወጪ ማዕቀፍን ማዘጋጀት፤
 • የክልላዊ እምቅ የገቢ ሀብትን የሚመለከቱ ጥናቶችን ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ያጠናል፤ግብረ መልስ ያዘጋጃል፤
 •  አዳዲስ ማዘጋጃ ቤታዊ ታክስ ጥናቶች ያከናውናል፣
 • ለጥናት የሚረዱ የፊስካል ፖሊሲና ገቢ መረጃዎች ያደራጃል ፣
 •  በፊስካል ፖሊሲ ጥናትና ክትትል አቅም ማጎልበት/ስልጠና፣ልምድ ልውውጥ/ ያደረጋል
 •  የገቢ ሪፖርት አመዘጋገብ ላይ (Revenue Chart of Account) በሚደረግ ዝግጅትና አፈጻጸም ማሻሻያ ጥናት በማካሄድ በባለድርሻ አካላት ያስተቻል እንዲሁም ተመሳሳይ የክልልና የፈደራል መድረኮች ላይ በመሳተፍ ግበአት ይሰጣል፤
 • የአስተዳደር እርከኖችንና የክልል ማዕከል ሴክተር መ/ቤቶች የወጪና የገቢ ጥናቶች አፈጻጸም ድጋፍ፣ ክትትልና ግምገማ ማድረግ፤
 •  ስልጠናዎችን በዳሰሳ ጥናት መሠረት በማድረግ የስልጠና ማንዋል ያዘጋጃል፣
 •  የፊስካል ፖሊሲ ከማመንጨት እና ከማስፈጸም አንጻር የፊስካል ፖሊሲ መመሪያ፣ደንብ በማዘጋጀት ያሰለጥናል ፣
 • የወጪና የገቢ ማሻሻያ ጥናቶችን፣ በጥናት ውጤቶቹ ላይም ተመስርቶ ማሻሻያዎቹ ተግባራዊ እንዲሆኑ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፣
 •  የባለሙያ አቅምን በመገንባት ጥራት ያለው የፊስካል ፖለሲና ገቢ መረጃ በማደራጀትና የክትትል ስርዓት ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፣
 •  የፊስካል ፖሊሲ ማስፈጸሚያ/መሳሪያ/ በጀት ኖርም/Budget Norm/ በማጥናት ማጸደቅ፣ አፈጻጸሙን ይከታትላል፣
 •  መንግስት ሊከተለው የሚገባውን የበጀት ጉድለት መጠንና አሸፋፈኑን በተመለከተ ጥናትና ክትትል ያደርጋል፣ ለፖሊሲ ውሳኔ የሚረዳ ሀሳብ ያመነጫል፣
 •  በክልሉ የመንግሥት ወጪን በመደበኛና ካፒታል እንዲሁም በዘርፍና በኢኮኖሚ (Functional and Economic) የሚኖራቸውን አፈፃፀም ይከታተላል፣
 •  ለዓመታዊ የመንግስት በጀት የሚቀርቡ የኢኮኖሚ መግለጫ ሰነዶችን እንዲሁም ዓመታዊ የበጀት ፖሊሲ መግለጫ ያዘጋጃል፤
 • መ/ቤቱ በፊሲካለ ፖሊሲ ጥናትና ክትትል በሚመለከት ከአገሪቱ የልማት አጋሮች የቴክኒክ ዕገዛ እንዲያገኝ ይሰራል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
 • በፊሲካል ፖሊሲ ጥናትና ክትትል የመ/ቤቱንም ሆነ የዞኖች፣ልዩ ወረዳዎች/ወረዳዎችና ከተማ አሰተዳደር አቅም የሚያጐለብቱ ተግባራትን ያከናውናል፣ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ሥልጠናዎችን ያፈላልጋል፣ ያዘጋጃል፣ ተግባራዊ እንዲሆኑም ይሰራል
 • የዳይሬክቶሬቱን ዓመታዊ፣ የሩብ ዓመት፣ የግማሽ ዓመት፣ የዘጠኝ ዓመት ዕቅድና የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶችን ለቅርብ ኃላፊና ለቢሮ በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ያቀርባል፣
 •  ዳይሬክቶሬቱን በሚመለከቱ በተለያዩ ስብሰባዎች፣ሴሚናሮች ላይ በመገኘት የልምድ ልዉዉጦችንና ግንዛቤ በመቀመር በዳይሬክቶሬት ሥር የሚገኙ ባለሙያዎችን ዉጤታማ የሆነ ሥራ እንዲያከናወኑ ማድረግ፣የተገልጋዮችን እርካታ ደሰሳ ጥናት እንዲካሄድ በማድረግ የዳይሬክቶሬቱን አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት የሚሻሻልበት ሁኔታ ይቀይሳል፣
 • በዳይሬክቶሬቱ የሰዉ ኃይል በመዋቅሩ መሠረት እንዲሟላ ያደርጋል፣
 • በዳይሬክቴሩ የሚያስፈልጉ የሥራ ቁሳቁሶች እንዲሟላ ያደርጋል፣
 • ስራውን ለማስፈፀም የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራቶችን ይፈጽማል፡፡
 • የክልል ማዕከል፣ የሴክትር መ/ቤቶችና የአሰተዳደር ዕርከኖች የመካከለኛና የአጭር ዘመን የፊዚካልና ፋይናንሻል ዕቅድ አዘገጃጀት ሂደትን ይከታተላል፤
 • በክልል ማዕከል፣ የሴክትር መ/ቤቶችና የአሰተዳደር ዕርከኖች ያዘጋጁትን ዓመታዊና መካከለኛ ዘመን ዕቅድ የክልሉን ሀብት መነሻ ማድረጋቸውን ይገመግማል ግብረ መልስ ይሰጣል፤
 • በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በክልሉ ሀብት አጠቃቀም ውጤታማነት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊፈጥሩ የሚችሉ በተበጣጠሰና ባልተመጋገበ መልኩ ባልተደራጀ ሁኔታ በተለያዩ የክልል ሴክተር መ/ቤቶች እና የስራ ክፍሎች የሚሰሩ ጥናቶችን በተቀናጀና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ ተቋማዊ በሆነ መንገድ እንዲከናወኑ ያደርጋል፤ ይከታተል፤ ድጋፍ ይሰጣል፣ይቆጣጥራል፤
 • የመንግስትና የግል ሽርክና/አጋሪነት/ የማጎልበት ስራዎችን ያከናውናል፣ ለስራ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፣ አሠራሮችንም ይዘረጋል፡ ያስተባብራል፤
 • በየአሰተዳደር ዕርከኖችና በክልል ማዕከል ሴክተር መ/ቤቶች በየተቋሙ ያሉ የስራ ክፍሎች ያሉባቸውን የጥናትና ምርምር ፍላጎቶች ወጥነት፣ ወጪ ቆጣቢና ዘላቂነት ባለው ተቋማዊ አግባብ እንዲመሩ ድጋፍ ይሰጣል፣ አፈጻጸሙን ይገመግማል ግብረ መልስ ይሰጣል፣
 • በክልሉ ባሉ የአሰተዳደር ዕርከኖችና ሴክተር መ/ቤቶች የሀብት አሰተዳደርና የበጀት አመዳደብ ስርዓት በክፍለተ ዘርፎች ማለትም በኢኮኖሚያዊ፣በማህበራዊና የአሰተዳደርና አገልግሎት አንፃር የተቀኘና ውስጣዊና ውጫዊ ስጋቶች/Risks/ ለመለየት፣ ለመለካትና የስጋት ማቅለያ ሃሳቦችን ማመንጨት የሚያስችል ዳሰሳ ጥናት በማካሄድ ግብረ መልስ ይሰጣል የማሻሻያ ሀሳቦችን ለሚመለከተው አካል ያቀረባል፣
 • በክልሉ ባሉ ባለበጀት መ/ቤቶችና የአሰተዳደር ዕርከኖች የሚከናወኑ የሪፎርም ስራዎች ፋይዳ ዳሰሳ ጥናት /impact assessment/ ባማካሄድ የክልሉ እምቅ ባገናዘበና ባመላከተ መልኩ መዘጋጀታቸውንና መፈጸማቸውን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፣ ለሚመለከታቸውም ሪፖርት ያቀርባል፤
 • የሪፎርም ስራውን በሚመለከት ከፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት የሚወጡ መመሪያዎች ፣ደንቦች እና ተጓዳኝ ህጎች ከክልሉ ሀብት ጋር ስለሚኖራቸው መስተጋብር በመመርመር ተግባራዊ እንዲሆን ያስደርጋል፣
 • በክልል ማዕከል እና አስተዳደር እርከኖች ተመሳሳይ በሆኑ የስራ ክፍሎች ለሚሰሩ አነስተኛ ጥናቶች የጥናት ስልቶች ዝግጅትና ትግበራ ሂደት ሙያዊ ድጋፍ ይሰጣል፣አፈጻጸሙንም ይከታተላል፡፡
 • በሀብት አስተዳደር ስርዓት እና ተግባራት አፈጻጸም ሂደት ላይ ቀጣይነት ያለው ተቋማዊ የመማማሪያና የልምድ ልውውጥ ስርዓትና ባህል እንዲጎለብት ያደርጋል፤
 • የስትራቴጂክ እቅድ አፈጻጸም ለማሳለጥ የሚያስችል የክትትልና የድጋፍ አግባብ እንዲጠናከር ለክልል ማዕከል፣ የሴክተር መ/ቤቶችና በየአስተዳደር እርከኑ ለሴክተር ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ይሰጣል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣
 • የዳይሬክቶሬቱን ዓመታዊ፣ የሩብ ዓመት፣ የግማሽ ዓመት፣ የዘጠኝ ዓመት ዕቅድና የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶችን ለቅርብ ኃላፊና ለቢሮ በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ያቀርባል፣
 • ዳይሬክቶሬቱን በሚመለከቱ በተለያዩ ስብሰባዎች፣ሴሚናሮች ላይ በመገኘት የልምድ ልዉዉጦችንና ግንዛቤ በመቀመር በዳይሬክቶሬት ሥር የሚገኙ ባለሙያዎችን ዉጤታማ የሆነ ሥራ እንዲያከናወኑ ማድረግ፣የተገልጋዮችን እርካታ ደሰሳ ጥናት እንዲካሄድ በማድረግ የዳይሬክቶሬቱን አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት የሚሻሻልበት ሁኔታ ይቀይሳል፣
 • በዳይሬክቶሬቱ የሰዉ ኃይል በመዋቅሩ መሠረት እንዲሟላ ያደርጋል፣
 •  በዳይሬክቴሩ የሚያስፈልጉ የሥራ ቁሳቁሶች እንዲሟላ ያደርጋል፣
 • ስራውን ለማስፈፀም የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራቶችን ይፈጽማል፡፡