ለዘርፉ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት ለመወጣት በስሩ በተደራጁት ዳይሬከተሮች አማካይነት ክልላዊና በየአሰተዳደር እርከኑን የመንግስት በጀት ያዘጋጃል፣ የበጀቱን አፈጻጸም ያስተዳደራል፣ ይገመግማል፤ ይቆጣጥራል እንዲሁም የክልሉ መንግስት የብድርና እርዳታ ስምምነቶችን ይፈራረማል፣ ያስተዳደራል፤ በኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት ዘርፍ የተሰማሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ስራ ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ያስተባብራል፣ ይቆጣጥራል፤ የሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች የፕሮጀክቶች የብቃት ምዘና ያደርጋል፣ የስራ ውል ይፈራረማል፣ ያስተባብራል፣ ይከታተላል ይገመግማል፡፡ ይህ ዘርፍ በስሩ የበጀት አስተዳደር፣ ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ፣የፊሲካል ማዕቀፍና የገቢ አሰባሰብ ክትትልና ግምገማ፣ የሲቪል ማኀበረሰብ ፕሮጀክቶች ጉዳይ ማሰተባበሪያ፣ የመንግስታት ትብብር ፕሮግራሞች ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬቶችንና በስራቸው ያሉ ቡድኖችን የሚያስተባበር ዘርፍ ሆነው ተደራጅቷል፡፡
- የበጀት ዝግጂትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
- የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የፕሮጀክቶች ጉዳይ ማስተባበሪያ
- የፊስክል ፖሊስና ገቢ ማበልጸግ ዳይሬክቶሬት
- የመንግስታት ትብብር ዳይሬክቶሬት