የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
- የግዥና ንብረት አስተዳደር ስራዎች ተመጋጋቢ በመሆናቸው እነኝህ ተዛማጅነት ያላቸው ስራዎች በአንድ የስራ ክፍል ከጫፍ እስከ ጫፍ ማከናወን ያስችላል፤ ተጠያቂነትም ያጠናክራል፣
- የግዥና የንብረት አስተዳደር መረጃ ፍሰትን ፈጣንና ግልፅ እንዲሆን ያደርጋል፣ ግዥ ከመከናወኑ በፊት ተቋሙ ያለውና የሌለውን ንብረት አረጋግጦ ግዥ ለመፈፀም ያስችላል፤ ያለውን ሃብት ይቆጣጥራል፣
- በእርዳታና ብድር ተገዝተው የሚመጡ ዕቃዎች በአግባቡ እንዲመዘገቡና ለአገልግሎት እንዲውሉ ያደረጋል፣
- የsS<” የዕቃዎችን፣ የግንባታ ስራዎችንና አገልግሎቶችን የግዥ ረቂቅ ውል ያዘጋጃል፣ በረቂቅ ውሉ ላይ ከአሸናፊ አቅራቢ ድርጅት ጋር ይወያያል፣ ስምምነት ላይ ይደርሳል፣ የውል ሰነዶች እንዲፈረሙ ያደርጋል፣ አቅራቢዎች በግዥ መመሪያው መሰረት ያቀረቡትን የውል ማስከበርያ ዋስትና ይይዛል፣ ያስተዳድራል፣
- የመተማመኛ ሰነድ (Letter of Credit) ማሻሻያ ጥያቄዎችን ተቀብሎ ምላሽ ይሰጣል፣
- አቅራቢው ድርጅት ኦሪጅናል እና ኮፒ የጭነት ሰነዶችን አሟልቶ መላኩን ይከታተላል፣ የጭነት ሰነድ ልዩነቶችን (Documents Discrepancy) የአገልግሎቱን ጥቅምና መብት በማይጎዳ መልኩ ተቀባይነት እንዲኖራቸው ያደርጋል፣
- የውል አፈጻጸም ልዩነት ሲያጋጥም የውል ማሻሻያዎችና የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ ሃሳብ ያቀርባል፣
- በውሉ መሰረት ለአቅራቢዎች ሊከፈል የሚገባ ክፍያ የተጠናቀቀ መሆኑንና ለተከፈሉ ክፍያዎች ተገቢው አገልግሎት መገኘቱን ይከታተላል ግብረ መልስ ይሰጣል፣
- ከሶስተኛ ወገኖች ማለትም ከኢንሹራንስ ድርጅቶች፣ ከአጓጓዥ ድርጅቶች፣ ከኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን፣ ከጉምሩክና ዕቃ አስተላላፊዎች፣ ከባንክ እና ከሌሎች አገልግሎት ሰጭዎች ጋር የተያያዙ የአገልግሎቱ ጥቅሞች መከበራቸውንና የአገልግሎቱ ግዴታዎች የተፈጸሙ መሆናቸውን ክትትል ያደርጋል፣
- አቅራቢ ድርጅቶች በውሉ መሰረት ዕቃዎችን፣ የግንባታ ዘርፍ ስራዎችንና አገልግሎቶችን ካላቀረቡ በውሉ መሰረት ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ የመፍትሄ ሃሳብ ያቀርባል፣
- የስራ ዕቅድና የአፈጻጸም ሪፖርት አዘጋጅቶ ያቀርባል፣
- የዳይሬክቶሬቱን ዓመታዊ፣ የሩብ ዓመት፣ የግማሽ ዓመት፣ የዘጠኝ ዓመት ዕቅድና የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶችን ለቅርብ ኃላፊና ለቢሮ በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ያቀርባል፣
- ዳይሬክቶሬቱን በሚመለከቱ በተለያዩ ስብሰባዎች፣ሴሚናሮች ላይ በመገኘት የልምድ ልዉዉጦችንና ግንዛቤ በመቀመር በዳይሬክቶሬት ሥር የሚገኙ ባለሙያዎችን ዉጤታማ የሆነ ሥራ እንዲያከናወኑ ማድረግ፣የተገልጋዮችን እርካታ ደሰሳ ጥናት እንዲካሄድ በማድረግ የዳይሬክቶሬቱን አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት የሚሻሻልበት ሁኔታ ይቀይሳል፣
- በዳይሬክቶሬቱ የሰዉ ኃይል በመዋቅሩ መሠረት እንዲሟላ ያደርጋል፣
- በዳይሬክቴሩ የሚያስፈልጉ የሥራ ቁሳቁሶች እንዲሟላ ያደርጋል፣
- ስራውን ለማስፈፀም የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራቶችን ይፈጽማል፡፡