• +251462204629
 • Hawassa , Ethiopia

የግብአት ፣ዐፈር ማዳበሪያና ተዘዋዋሪ ፈንዶች ክትትልና ግምገማ ቡድን

 • በደቡብ ገበሬዎች ህብረት ስራ ፌዴሬሽን እና በሃያ ዩኒየኖች ሥር በሚገኙ የአፈር ማዳበሪያ አያያዝና አጠባበቅ ሥርጭት ኦዲት ያከናውናል፣
 • ከማዕከላዊ መጋዘን ወደ ማሰራጫ ጣቢያ አፈር ማዳበሪያ የሚያጓጉዙ የትራንስፖርት ድርጅቶች ማህበራት በመንግስት የግዥ አፈጻጸም ደንብና መመሪያ መሠረት የመጓጓዣ ዋጋ የተከፈላቸው መሆኑን ኦዲት ማድረግ
 • በደቡብ ገበሬዎች ህብረት ስራ ፈዴሬሽን እና ከዩኒየኖች በምርት ዘመኑ ወደ ወረዳና በከተማ ቀበሌአት /ጣቢያ/ መጋዘን ገቢ የተደረገ የአፈር ማዳበሪያ ኦዲት ያደረጋል፤
 • ለአርሶ አደሮች የተሰራጨ የአፈር ማዳበሪያ ኦዲት ያከናዉናል፣
 • የእጅ በእጅ ሽያጭ የቅድመ ክፍያና የብድር ተመሻ የአፈር ማዳበሪያ ገንዘብ ኦዲት ያከናዉናል፤
 • በኦሞ ኤጀንቶች ተሰብስቦ ለኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ንዑስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ገቢ የተደረገ የአፈር ማዳበሪያ ሽያጭ ገቢ ኦዲት ያደረጋል፤
 • በኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ንዑስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አማካኝነት ለአፈር ማዳበሪያ ሽያጭ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር ገቢ የተደረገ ገንዘብ ኦዲት ያከናውናል፤
 • የአፈር ማዳበሪያ ሽያጭ የውል አስተዳደርና አፈጻጸም ህጋዊነትን ኦዲት ያደረጋል፤
 • የአፈር ማዳበሪያ የገቢና የወጪ ደረሰኞች ስርጭትና አጠቃቀም ኦዲትያደረጋል፤
 • ካለፈው ምርት ዘመን በመጋዘን ውስጥ ሳይሰራጭ ያደረ የአፈር ማዳበሪያ ቆጠራ ያከናዉናል፣
 • በየአስተዳደር እርከኑ ለሚገኙ ሴክተር ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ይሰጣል፤
 • የዳይሬክቶሬቱን ዓመታዊ፣ የሩብ ዓመት፣ የግማሽ ዓመት፣ የዘጠኝ ዓመት ዕቅድና የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶችን ለቅርብ ኃላፊና ለቢሮ በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ያቀርባል፣
 • ዳይሬክቶሬቱን በሚመለከቱ በተለያዩ ስብሰባዎች፣ሴሚናሮች ላይ በመገኘት የልምድ ልዉዉጦችንና ግንዛቤ በመቀመር በዳይሬክቶሬት ሥር የሚገኙ ባለሙያዎችን ዉጤታማ የሆነ ሥራ እንዲያከናወኑ ማድረግ፣የተገልጋዮችን እርካታ ደሰሳ ጥናት እንዲካሄድ በማድረግ የዳይሬክቶሬቱን አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት የሚሻሻልበት ሁኔታ ይቀይሳል፣
 • በዳይሬክቶሬቱ የሰዉ ኃይል በመዋቅሩ መሠረት እንዲሟላ ያደርጋል፣
 • በዳይሬክቴሩ የሚያስፈልጉ የሥራ ቁሳቁሶች እንዲሟላ ያደርጋል፣
 • ስራውን ለማስፈፀም የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራቶችን ይፈጽማል፡፡