የደቡብ ክልል ፋይናንስ ቢሮ አመራሮችና ሠራተኞች ለጀግናው መከላከያ ሠራዊት የሚሆን ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጋ የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ
አረመኔው የህወሃት አሸባሪ ቡድን በሰሜን ዕዝ መካላከያ ሠራዊት አባላት ላይ ያደረሰውን እኩይ ተግባር ለመመከት የሚደረገው ህግን የማስከበርና የህልውና ዘመቻ በመደገፍ የቢሮው አመራሮችና ሠራተኞች ወደ 500 ሺህ ብር ድጋፍ አደረጉ።ለመከላከያ ሠራዊት የሚደረገውን የድጋፍ መርሀ-ግብር ምላሽ ለመሰጠት መላው የቢሮው አባላት ባደረጉት ውይይት ከወር ደመወዛቸው የሚቆረጥ የገንዘብ ድጋፍ ከመስጠት ባሻገር ማናቸውንም ጥሪ በመቀበል የህይወት መስዋዕተትነት እስከመክፈል ድረስ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል ።አያይዘውም ለሀገር ጋሻና መከታ በሆነው ሠራዊት ላይ አሸባሪው የወያኔ ቡድን የፈጸመውን ኢ-ሰብአዊ ድርጊት እጅጉን እንደሚቃሙና ይህን አጸያፊ ተግባር መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈፀመው ከዲው ቡድን ለፍርድ እንዲቀርብ ጠይቀዋል።
0