የውስጥ ኦዲት ድጋፍ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት
- የፋይናንሻያልና የህጋዊነት ኦዲት ከሚደረጉ መ/ቤቶች እና የሥራ ዘርፎች ጋር የኦዲት መግቢያ ውይይት ያደረጋል፣ ከኦዲቱ ጋር አግባብነት ያላቸው መረጃዎችን በመሰብስብ ያደራጃል፣ የፋይናንሻያልና የህጋዊነት ኦዲት ያከናዉናል፣
- የገቢ፣ የወጪ፣የዝውውር ፣ የተከፋይ፣ የተሰብሳቢ፣ የሳጥንና የባንክ ሂሳቦች የውስጥ ቁጥጥር ስርዓቱን በመገምገም ኦዲት ያከናዉናል፤
- የበጀት አስተዳደርና ቁጥጥር ኦዲት ይሰራል፤
- የአስተዳደራዊ ስራዎች ኦዲት ይሰራል፣
- የንብረት አስተዳደር ኦዲት ያደርጋል፣
- በበጀት ዓመቱ መጨረሻ የጥሬ ገንዘብና ንብረት ቆጠራ በማድረግ ፈሰስ እንዲሆኑ ያደርጋል፤
- የውስጥ ቁጥጥር ስርዓት ውጤታማነት ይገመግማል፤
- አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ልዩ ኦዲት ያደርጋል፣
- የብድርና የዕርዳታ /ልዩ ልዩ ፈንድ/ ሂሳቦች ኦዲት ያደርጋል፣
- በኦዲት ውጤት መነሻ ለፍትህ አካላት የሙያ ምስክርነት ይሰጣል፣
- የፋይዳ ዳሰሳ ጥናት ያደርጋል፣
- ድጋፍ ክትትልና ግምገማ ያደርጋል፣
- የተሽከርካሪ ነዳጅ አጠቃቀም ኦዲት ያደረጋል
- የንብረት አስተዳደር ፣የህትመት ፣የመፅሐፍት የመድሃኒት እና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች ኦዲት ያከናውናል፣
- ቋሚና የአላቂ ዕቃዎች ኦዲት ያደረጋል
- ኦዲት ሪፖርት ጥራት ግምገማ ማድረግና ግብረ መልስ መስጠትና በኦዲት ግኝቶች ላይ የእርምት እርምጃ ስለመወሰዱ ክትትል ያደረጋል፤
- በየአስተዳደር እርከኑ ለሚገኙ ሴክተር ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ይሰጣል፤
- የዳይሬክቶሬቱን ዓመታዊ፣ የሩብ ዓመት፣ የግማሽ ዓመት፣ የዘጠኝ ዓመት ዕቅድና የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶችን ለቅርብ ኃላፊና ለቢሮ በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ያቀርባል፣
- ዳይሬክቶሬቱን በሚመለከቱ በተለያዩ ስብሰባዎች፣ሴሚናሮች ላይ በመገኘት የልምድ ልዉዉጦችንና ግንዛቤ በመቀመር በዳይሬክቶሬት ሥር የሚገኙ ባለሙያዎችን ዉጤታማ የሆነ ሥራ እንዲያከናወኑ ማድረግ፣የተገልጋዮችን እርካታ ደሰሳ ጥናት እንዲካሄድ በማድረግ የዳይሬክቶሬቱን አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት የሚሻሻልበት ሁኔታ ይቀይሳል፣
- በዳይሬክቶሬቱ የሰዉ ኃይል በመዋቅሩ መሠረት እንዲሟላ ያደርጋል፣
- በዳይሬክቴሩ የሚያስፈልጉ የሥራ ቁሳቁሶች እንዲሟላ ያደርጋል፣
- ስራውን ለማስፈፀም የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራቶችን ይፈጽማል፡፡