• +251462204629
  • Hawassa , Ethiopia

የክፍያና ሂሳብ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

  • የተቋሙን የፀደቀ በጀት በበጀት ዓይነት በየባለበጀት መ/ቤቶችና በሥራ ክፍሎች በመለየት በፋይናንስ ምንጭ፣ በበጀት ዓይነትና በወጪ መደብ በመለየት ሌጀር በማቋቋም ይመዘግብል፣ ከሥራ ክፍሎች በዕቅዳቸው መሠረት የተዘጋጀውን የዓመቱን የጥሬ ገንዘብ ፍላጎት ዕቅድ በመሰብሰብ ማጣራትና ከፀደቀና ከቀሪ በጀት ጋር ያነጻጽራል፣ የፀደቀ በጀት መነሻ በማድረግ የጥሬ ገንዘብ ፍላጎት ዕቅድ በመደበኛና በካፒታል እንዲሁም በደመወዝና በሥራ ማሰኬጃ ለይቶ በማዘጋጀት ለመ/ፋ/አስ/ዋና የሥራ ሂደት ያቀረባል፤
  • የድጎማ ገቢ ለመመዝገብ የባንክ ክሬዲት አድቫይስ እና የጥሬ ገንዘብ ዝውውር ደብዳቤ ይሰበስባል፣ ለድጎማ ገቢ የገቢ ደረሰኝ ያዘጋጅል፤ ልዩ ልዩ ገቢዎችን የገቢ ደረሰኝ በማዘጋጀት ጥሬ ገንዘብ በመቀበል መዝገብ ላይ በመመዝገብ ወደ ባንክ በመውሰድ ገቢ ያደረጋል፣ ባንክ ገቢ ለተደረገው የክፍያ ሰነድ በማዘጋጀት ያፀድቃል፣ በጥሬ ገንዘብ መዝገብ ላይ ወጪውን በመመዝገብ የገቢና የክፍያ ሰነዶችን በመሂ-42 በዝርዝር በመመዝገብ ለሂሳብ ምዝገባና ሪፖርት ያቀረባል፤
  • የተቋሙን የክፍያ ጥያቂዎች አግብብነት በማጣራትና በጀት መኖሩን በማረጋገጥ አሰራሩን በተከተለ ሁኔታ ክፍያ /ከሳጥን ወይም ከባንክ/ ይገፅማል፤ የክፍያ ሰነድ ያወዳድቃል፤
  • የተቋሙን የደመወዝ፣ የሥልጠና /ስብሰባ የውሎ አበል፣ የትራንስፖርት እና የግዥ የክፍያ ጥያቄ ማስረጃዎችን/ጨረታ ሰነዶች አሰራሩን በተከተለ ሁኔታ በማጣራት ክፍያ ይፈፅማል፤ አፈጻጸሙን ይገመግማል
  • የተቋሙን የደመወዝና ሥራ ማስኬጃ ወጪ መርጃ ሪፖርት ለመንግሥት ፋይናንስ ያቀረባል፤ የበጀትና የወጪ ንጽጽር ሪፖርት ለስራ ክፍሎች ያቀረባል፤የፋይናንስ አፈፃፀም ሪፖርት በማዘጋጀት ለመ/ቤቱ ማናጅመንት በማቅረብ እንዲገመገም ያደረጋል፤
  • የችሮታ ጊዜ ክፍያ ጥያቄ በመቀበል ማስረጃ በማጣራትና በጀት መኖሩን በማረጋገጥ ክፍያ ይፈፅማል፣
  • የሣጥን የጥሬ ገንዘብ ቆጠራ ያካሂዳል፣የሳጥን የጥሬ ገንዘብ ገቢና ወጪ ሂሳብ ያመዛዝናል፣ የጥሬ ገንዘብ ቆጠራ ሰርተፊኬት በማዘጋጀት ይፈራረማል፣
  • የተቋሙን ለሚዛወሩ ሠራተኞች ክሊራንስ ከመንግሥት ዕዳ ነፃ መሆኑን በማረጋገጥ ይሰጣል፣ የአደራ/የተከፋይ ሂሳቦች ገቢና ወጪ ያስተዳደራል፣የልዩ ልዩ ፈንድ ሂሳቦች ገቢ መርምሮ በመቀበል ያስተዳደራል፤
  • የገቢ ሂሳብ በበጀት ዓይነትና በበጀት ምንጭ ፣የመደበኛና የካፒታል፤ የደመወዝና የሥራ ማስኬጃ ወጪ፣ የተለያዩ የወጪ ሂሳቦችን በበጀት ዓይነትና በበጀት ምንጭ እንዲሁም በመሥሪያ ቤት፣ በሥራ ሂደትና በወጪ መደብ በመለየት፤ የገቢ፣ የተሰብሳቢ፣ የተከፋይ የሂሳብ፣ ማመዛዘኛ ሂሳብ እና የባንክ ሂሳብ ለማስታረቅ የሂሳብ ሰነዶችን በመረከብና ምዝገባ በማከናወን ያሰተዳድራል፣
  • የተቋሙን ዓመታዊ ሂሳብ የቋሚና የጊዜያዊ ሂሳቦችን በመለየት የሂሳብ መዝጊያ ሂሳብ መዝገብ ላይ በመመዝገብ እና የድህረ ሂሳብ ማመዛዘኛ ምዝገባ ማካሄድ እንዲዘጋ ያደረጋል፤
  • የተቋሙን ተመዘግበው የተጠናቀቁ፣ የተመዘገቡ የበጀት ዝውውር፣ የገቢ ሂሳብ ማስረጃ ደረሰኞች ፣የባንክ አድቫይሶችና ደብዳቤዎች፣ በበጀት የተደገፉና የአደራ ተከፋይ ወጪ /ክፍያ/ የዝውውር ደረሰኞችን፣ የጥሬ ገንዘብ ነክ ያልሆኑ የገቢና ወጪ ሂሳቦች ምዝገባ የተከናወነበት ደረሰኞች /ሠነዶችን/፣ መዛግብቶችን አጠቃላይ እና ተቀጽላ የሃሳብ ሌጀሮችን፣ የገቢ፣ የወጪ፣ የተስብሳቢ፣ የተከፋይ፣ የዝውውር፣ የሂሳብ ማመዛዘኛዎች፣ የባንክ ሂሳብ ማስታረቂያ፣ የባንክ ሂሳብ መግለጫ/Bank statements/፣ የመደበኛና የካፒታል በጀት የባንክ ሂሳብ መግለጫ፣ የልዩ ልዩ ፈንዶችና የአደራ ተከፋይ ባንክ ሂሳቦች እንቅስቃሴ መግለጫዎች፣ የዋናው ግምጃ ቤት የሂሳብ ሠነዶች አደራጅቶ ይይዛል፣ ያስተዳድራል፤
  • በውጪ ኦዲተር የገቢ ወጪ ሂሳብ እንቅስቃሴ የሚገልጹ ዋና ሠነዶች፣ መዛግብቶች፣ ሌጀሮች፣ ሪፖርቶች፣ የፀደቀ በጀት፣ የበጀት ዝውውሮች፣ የተጨማሪ በጀት ዋና መረጃዎችና ደጋፊ ማስረጃዎች አቅርቦ ያስመረምራል፣ ለተገኙ ግኝቶች የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፣
  • የዳይሬክቶሬቱን ዓመታዊ፣ የሩብ ዓመት፣ የግማሽ ዓመት፣ የዘጠኝ ዓመት ዕቅድና የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶችን ለቅርብ ኃላፊና ለቢሮ በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ያቀርባል፣
  • በዳይሬክቶሬቱ የሰዉ ኃይል በመዋቅሩ መሠረት እንዲሟላ ያደርጋል፣
  • በዳይሬክቴሩ የሚያስፈልጉ የሥራ ቁሳቁሶች እንዲሟላ ያደርጋል፣
  • ስራውን ለማስፈፀም የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራቶችን ይፈጽማል፡፡