የክዋኔ ኦዲት ዳይሬክቶሬት
- የክዋኔ ስልጠና ፣ የኦዲት ሙያ ድጋፍ እና ምክር አገልግሎት ጥያቄ እንደ ግብዓት በመቀበል የዳሬክቶሬቱን ዕቅድና የአፈጻጸም ሪፖርት ያዘጋጃል፣
- የኦዲት ፕሮስጀር ሰነድ እና መመሪያ ለማዘጋጀት መረጃዎችን በመሰብስብና በመተንተን የኦዲት የፐሮስጀር ሰነድና መመሪያ ያዘጋጃል፣ስልጠና በመስጠት፣ የፕሮግራሞችና የፕሮጀክቶች ቅልጣፌና ውጤታማነት ፣ገንዘብ ያስገኘው ፋይዳ /value for money audit/ የአካባቢ ተስማሚነትና ብክለት አዋጭነት (Economical Value ) ኦዲት ያደረጋል፣
- የኦዲት ሙያ ድጋፍና ምክር አገልግሎት ይሰጣል ፤የክዋኔ ኦዲት የፕሮስጀር አፈጻጸም የውጤት ጥራትና የውስጥ ቁጥጥር ስርዓት ይገመግማል፣ ይከታትላል ፤
- የክዋኔ ልዩ ኦዲትን በማከናወን በፍትህ አካላት ሲጠየቅ ፈጣን የሙያ ምስክርነት አገልግሎት ይስጣል፤ የተገኘውን ፋይዳ በዳሰሳ ጥናት ያረጋግጣል፣
- የፀደቀ የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት፣ የኦዲት ፕሮስጀርና የስልጠና ሰነድ የተሰጠ ስልጠና የሙያና የምክር አገልግሎት የተደረገ ድጋፍ እንዲሁም የተሰጠ የሙያ ምስክርነት ያሰገኘውን ውጤት ይገመግማል፣ የተገኘውን ተሞክሮ በመቀመር የኦዲት ሽፋኑን፣ አፈጻጸሙን፣ ለማሳደግ የሀብት አጠቃቀም ውጤታማነትን፣ የአካባቢ ብክለትና የብዝሀ ሀብት መሻሻል እና የተጠያቂነትን አሰራር ለማስፈን ይሰራል፤
- ከውጭና ከውስጥ ኦዲት የቀረበ የኦዲት ሪፖርት ጥራት በመገምገምና ግብረ መልስ በመስጠትና በግኝቶች ላይ የእርምት እርምጃ ስለመወሰዱ ክትትል ያደርጋል፣
- የዳይሬክቶሬቱን የዕቅድ ዝግጅትና የአፈጻጸም ሪፖርት ያዘጋጃል፣
- በየአስተዳደር እርከኑ ለሚገኙ ሴክተር ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ይሰጣል፤
- የዳይሬክቶሬቱን ዓመታዊ፣ የሩብ ዓመት፣ የግማሽ ዓመት፣ የዘጠኝ ዓመት ዕቅድና የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶችን ለቅርብ ኃላፊና ለቢሮ በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ያቀርባል፣
- ዳይሬክቶሬቱን በሚመለከቱ በተለያዩ ስብሰባዎች፣ሴሚናሮች ላይ በመገኘት የልምድ ልዉዉጦችንና ግንዛቤ በመቀመር በዳይሬክቶሬት ሥር የሚገኙ ባለሙያዎችን ዉጤታማ የሆነ ሥራ እንዲያከናወኑ ማድረግ፣የተገልጋዮችን እርካታ ደሰሳ ጥናት እንዲካሄድ በማድረግ የዳይሬክቶሬቱን አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት የሚሻሻልበት ሁኔታ ይቀይሳል፣
- በዳይሬክቶሬቱ የሰዉ ኃይል በመዋቅሩ መሠረት እንዲሟላ ያደርጋል፣
- በዳይሬክቴሩ የሚያስፈልጉ የሥራ ቁሳቁሶች እንዲሟላ ያደርጋል፣
- ስራውን ለማስፈፀም የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራቶችን ይፈጽማል፡፡