• +251462204629
  • Hawassa , Ethiopia

የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ሴክተሩ የተጣለበትን ሀብት የማስተዳደር ኃላፊነት በብቃት መወጣት እንዲችል የድርሻውን እያከናወነ ይገኛል

በክልሉ ፋይናንስ ቢሮ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት የሴክተሩን ተልዕኮ ለማሳካት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል፡፡ በዚህም መሠረት የIBEX ዳታቤዝ ችግር ያለባቸውን በዘላቂነት ለመፍታት ዳታቤዛቸው የማስተካከል የውስጥ ኔትወርክ ያላቸውን ወደ ረዳኔት መሠረተ ልማት ሥርዓት የማስገባት ሥራ ተሠርቶ በ2011 በጀት ዓመት ከነበረው 115 የወረዳኔት ተጠቃሚዎች ላይ ተጨማሪ 35 ዞኖችና ወረዳዎች በማስገባት በድምሩ 150 መ/ቤቶች /Online/ እንዲሰሩ ተደርጓል፡፡ ይህም በዳታቤዝ ላይ የሚደርሱ መበላሸትና መረጃ መጥፋት ከማስቀረቱም በላይ ሪፖርት በወቅቱ እንዲቀርብ ማድረግና በየመሥሪያ ቤቶቹ የሚታዩ የሂሳብ ችግሮችን በወቅቱ ተከታትሎ ድጋፍ ለማድረግና ለመፍታት አስችሏል፡፡

ከመንግስት ፋይናንስ ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት በዞንና ልዩ ወረዳዎች እንዲሁክ ችግር አለባቸው በተባሉ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ በመገኘት እንዲሁም ሂሳብ ለመዝጋት ወደ ክልል ለመጡ የሂሳብ ባለሙያዎች ድጋፍ በማድረግ የ2011 በጀት ዓመት ሂሳብ በተሻለ ጥራትና በስታንዳርዱ መሠረት መዝጋት ተችሏል።
የክልሉ ምክር ቤት በወሰነው የዞኖች አዲስ አደረጃጀት መሠረት በነባር ዞኖች ውስጥ የነበሩትን ወረዳዎችና አዲስ የተጨመሩ ወረዳዎችን በማካተት የዞኖች መከፈልና በፋይናንሻል ሥርዓቱ ወይም በIBEX ላይ የማስተካከልና የወረዳዎች የማሸጋሸግ ሥራ ተሰርቷል፡፡ እነዚህም:—
 በጋሞጎፋ ዞን ውስጥ የነበሩትን መዋቅሮች ወደ ጋሞና እና ጎፋ ዞኖች
 በቤንች ማጂ ውስጥ ዞን የነበሩትን መዋቅሮች ወደ ቤንች ሸኮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች
 የሰገን አካባቢ ዞን ውስጥ የነበሩትን ወረዳዎች ወደ ኮንሶ ዞንና እና ልዩ ወረዳዎች መዋቅር
 እንዲሁም በልዩ ወረዳ መዋቅር ውስጥ የነበረውን የሃላባ ልዩ ወረዳ የከተማ አስተዳደሩን ከአዲስ ወረዳዎችን አካቶ በአዲስ ዞን መዋቅር የማደራጀት በIBEX ሥርዓት ላይ የማስተካከል ሥራ ተሠርቷል፡፡
 በቢሮው ዳይሬክቶሬቶችና የክልል መሥሪያ ቤቶችና በIBEX፣ በኔትወርክ እና በፔሮል በቀረቡ የድጋፍ ጥያቄዎች ምላሽ እየተሰጠ ሲሆን በወረዳኔት ተጠቅመው በቀጥታ /Online/ ከሚሰሩ መሥሪያ ቤቶች የቀረቡ 247 የማስተካከያ ጥያቄ በዳታቤዝ ላይ ድጋፍ ተደርጓል፡፡
 የሁሉም የቻናል አንድ ፕሮጀክቶች ሂሳብ በሁሉም የአስተዳደር ዕርከን በIBEX እንዲከናውን የተደረገ ሲሆን በዘንድሮው ዓመት አዲስ የተቋቋመው የUIID ተጠቃሚ ከተሞችና አዲስ ወደ ልማታዊ ሴፍቲኔት የገቡ ወረዳዎች ለ102 ወንድና ለ37 ሴት በድምሩ ለ139 የሂሳብ ባለሙያዎች የIBEX ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡
 በሴክተሩ የሚከናወኑ ተግባራት በቴክኖሎጂ እንዲደገፉ ጥረት ሲደርግ የቆየ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም ከገጠመን የCOVID-19 ወረርሽኝ ምክኒያት አካላዊ ስብሰባዎችን በማስቀረት በቴክኖሎጂ /በቪዲዮ ኮንፈረንስ/ ውይይቶችን ለማድረግ ለኃላፊዎች ዙም/Zoom/ የሚባል ሶፍትዌር በመጫንና በመደገፍ ላይ ይገኛል፡፡
 በበጀት ዓመቱ በዕቅድ ተይዘው የነበሩ እንዲሁም አሁን በCOVID-19 ምክኒያት ለገጠመን ችግርም ትልቅ መፍትሔና ዕገዛ ማድረግ የሚችሉ ሲስተሞችን ወደ ትግበራ ለማስገባት ዳይሬክቶሬቱ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል፡፡
የIBEX ዳታቤዝ ችግር ያለባቸውን በዘላቂነት ለመፍታት ዳታቤዛቸውን የማስተካከል የውስጥ ኔትወርክ ያላቸውን ወደ ወረዳኔት መሠረተ ልማት ስርዓት የማስገባት ሥራ ተሰርቶ በ2012 በጀት ዓመት ከነበረው 115 የወረዳኔት ተጠቃሚዎች ላይ ተጨማሪ 35 ዞኖችና ወረዳዎች በማስገባት በድምሩ 150 መስሪያ ቤቶች /online/ እንዲሰሩ ተደርጓል፡፡ ይህም በዳታቤዝ ላይ የሚደርሱ መበላሸትና መረጃ መጥፋት ከማስቀረቱም በላይ ሪፖርት በወቅቱ እንዲቀርብ ማድረግና በየመሥሪያ ቤቶቹ የሚታዩ የሂሳብ ችግሮች በወቅቱ ተከታትሎ ድጋፍ ለማድረግና ለመፍታት አስችሏል፡፡
የonline ተጠቃሚዎችን ሥራ የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ እንዲቻል የሁሉንም መስሪያ ቤቶች የኔትወርክ አቅም በእጥፍ እንዲያድግ ተደርጎ የዘመኑን ቴክኖሎጂ በመጠቀም በማንኛውም ሰዓትና ቦታ በስልክ የሚቀርቡ የድጋፍ ጥያቄዎች በወቅቱ ለመመለስ ሥርዓት ተዘጋጅቶ አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል፡፡

0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *