የኢንስፔክሽንና የዉስጥ ኦዲት ዘርፍ
ኢንስፔክሽንና የውስጥ ኦዲት ዘርፍ ተወካይ መልዕክት
የመንግስት መ/ቤቶች ለተቋቋሙበት ዓሊማ ለተሰጣቸው ተሌዕኮ ማስፈጸሚያ የሚመደብሊቸው ሀብት በአግባቡ ለፀደቀው ዓሊማ ብቻ በቁጠባ፣ በብቃት እና በውጤታማነት በመፈጸም ግሌፅነትና ተጠያቂነት በማረጋገጥ መሌካም አስተዳደር እንዲሰፍን የበኩሊቸውን ድርሻ ልወጡ ይገባል። በለላ በኩልም የመ/ቤቱ ተልዕኮና ግብ እንዲሳካ የራሱ የሆነ እገዛ የሚያደርግ ተጨማሪ እሴት የሚፈጥር ከተጽህኖ ነፃና ገለልተኛ የሆነ ማረጋገጫና የሙያ ምክር አገልግሎት ተግባር የሚያከናውን በእውቀትም በክህልትም ብቁ የሆነ ኦዲተር ሉመደብ ይገባሌ።በተጨማሪም በኦዲት ግኝቶች እንዲታረሙ በማድረግ በቀጣይም ውስን የሆነውን የመንግስት ሀብት ለብክነት ፣ለምዝበራና ለብሌሹ አሰራር እንዳይጋሇጥ ሥራችንን በወጡት የፋይናንስ አስተዳደር ህጎችና መመሪያዎችን መሠረት በኃሊፊነትና በባለቤትነት ስሜት በብቃት እድንወጣ አሳስባለሁ።
ለዘርፉ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት ለመወጣት ባለ በጀት መ/ቤቶች ውስጥ የሚገኙ የውስጥ ኦዲተሮችን ማደራጀትና የአቅም ግንባታ ስራዎችን ማከናወንን የሚያካትት ሲሆን በስሩ በተደራጁት ዳይሬከተሮች አማካይነት የክልሉን መንግስት የፋይናንስና ንብረት ኢንስፔክሽን ማከናወን፣ እርምጃ መውሰድና እንድወስድ ማድረግ ተግባራቶችን ያከናውናል፡፡ይህ ዘርፍ በስሩ የክዋኔ ኦዲት፣የፋይናንሻልና የንብረት ኦዲትና የግበዓት፤የአፈር ማዳበሪያና የተዘዋዋሪ ፋንዶች ኦዲት ዳይሬክቶሬቶች የሚያስተባበር ዘርፍ ሆነው ተደራጅቷል፡፡
በዘርፉ የሚፈጸሙ ዋና ዋና ተግባራቶች
- የአፈር ማዳበሪያ ሥርጭትና ብድር አመላለስ፣ የከተማ እና የገጠር ወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ ተዘዋዋሪ ፈንድ ኦዲት ሥራ፣ የእንሰሳት መድሃኒትና የህክምና መሳሪያዎች ኦዲት ሥራ እና የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን ከአርሶ አደሩ የሚሰበሰብ የገቢ ሂሳብ ኦዲት ያከናውናል፣ ኦዲት ግኝት እርምጃ እንዲወስድ ያደረጋል፤ አፈጻጸሙን ይከታትላል፣ ይገመግማል
- በክልሉ የመንግስት ተቋማት በስራ ላይ የሚያውሉት ሀብት በቁጠባ (Economically)፣ በብቃት (Efficiently) እና ውጤታማ(Effectively) በሆነ መልኩ የአካባቢ ጥበቃን /Environmently/ ታሳቢ በማድረግ ማከናወናቸው እና ገንዘብ ያስገኘው ፋይዳ /value for money audit/ ኦዲት ያደረጋል፣
- በክልሉ መንግስት የበጀት ዋስትና የአፈር ማዳበሪያ በግዥ ቀርቦ ለተጠቃሚዎች እጅ በእጅ ክፍያ እና በብድር የሚሰራጭ የአፈር ማዳበሪያ አያያዝና አጠባበቅ፣ የሽያጭ ገንዘብ አሰባሰብና የብድር አመላለስ ኦዲት ያከናውናል፣ ግብረ መልስ ይስጣል፣
- ከፌዴራል መንግስት የሚላክ የከተማና የገጠር ወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ ተዘዋዋሪ ፈንድ፣ከአርሶ አደር የሚሰበሰብ የማህበራዊ ጤና መድን ገቢ ፣የትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮጀክት/GEQIP-II/፣ ዋን ዋሽ ፕሮግራም /One Wash/፣ኮ ዋሽ ፕሮግራም /Co-Wash/ ፣በገጠር የልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም / PSNP-4/ ፣የከተማ ልማታዊ ሴፍትኔት /UPSNP-4/፣ የመሠረታዊ አገልግሎት ማሻሻያ ፕሮጀክት /PBS-III/FTA/፣ የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር ፕሮጀክት /PFM/፣የመሬት ይዞታና ሰርትፍኬት ፕሮግራም /LIFT/ Land Information for Transformation/፣ ሀብት ኦዲት ያከናውናል፣ አፈጻጸሙን ይከታትላል፣ ይገመግማል፣
- የእንሰሳት መድሃኒቶችና ሽያጭ ገቢና የህክምና መሳሪያዎች ኦዲት ያደረጋል፣
- ከጠቅላይ ዐቃቤ ህግ፣ ከፍርድ ቤቶች እና ከህዝብ ምክር ቤቶች በልዩ ትዕዛዝ የሚሰጡ የኦዲት ሥራዎች ጥያቄ ተቀብሎ ኦዲት ያከናዉናል፣ የኦዲት ግኝቶች ላይ ማብራሪያ ይሰጣል፣ አፈጻጸሙን ይከታትላል፣
ዘርፉ የተሰጡትን ሀላፊነቶችን ለመወጣት በስሩ በሶስት ዳይሬክቶሬቶች ማለትም የፋይናሻያልና ንብረት ኦዲት፣ የክዋኔ ኦዲት፣ የግበአት፣የአፈር ማዳበሪያና የተዘዋዋሪ ፈንዶች ኦዲት ዳይሬክቶሬቶች ተደራጅቷል፡፡