- ዘርፉ ተጠሪነቱ ለመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ሆኖ የሚከተሉት ተግባራትና ኃላፊነቶች ይኖሩታል፡፡
- በሥሩ የተደራጁትን ዳይሬክቶቶችና ሌሎች የስራ ክፍሎች በበላይነት ይመራል፣
- የዘርፉን ዕቅድ በማዘጋጀት በስሩ ለሚገኙ ዳይሬክቶሬቶችና ሌሎች የስራ ክፍሎች ያወያያል፣ ስምምነት የተደረሰበትን የተግባርና የበጀት ዕቅድ ለማኔጅመንት አቅርቦ ያፀድቃል፣ የጸደቀውን ዕቅድና በጀት በስሩ ለተደራጁ ዳይሬክቶሬቶችና ሌሎች የስራ ክፍሎች ፍትሀዊ በሆነ መልኩ በማውረድ የአፈጻጸም ስምምነት ይፈራረማል፣
- የተቋሙን የሰው ሀብት ስራ አመራር ተግባራትን በተዘረጋው የአሰራር ስርዓት መሠረት አፈጻጸም ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ግብረ-መልስ ይሰጣል፣ ለቢሮ ኃላፊ ሪፖርት ያቀርባል፣
- የተቋሙን የግዥ/ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ተግባራትን በፋይናንስ ህግ መሠረት አፈጻጸም ይከታተላ፣ ይገመግማል፣ ግብረ-መልስ ይሰጣል፣ ለቢሮ ኃላፊ ሪፖርት ያቀርባል፣
- የተቋሙን የዕቅድና በጀት ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ተግባራትን በተዘረጋው የአሰራር ስርዓት መሠረት አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ግብረ-መልስ ይሰጣል፣ ለቢሮ ኃላፊ ሪፖርት ያቀርባል፤
- የተቋሙን የስርዓተ-ጾታ ሜይንስትሪሚንግ፣ የኤች አይ ቪ ሜይንስትሪሚንግ እና የሪከርድና ማህደር ስራ አመራር ተግባራትን በተዘረጋው የአሰራር ስርዓት መሠረት አፈጻጸሙን ይከታተላል ይገመግማል፣ ግብረ-መልስ ይሰጣል፣ ለቢሮ ኃላፊ ሪፖርት ያቀርባል፣
- በስሩ የሚገኙትን ዳይሬክቶሬቶች፣ ሌሎች የስራ ክፍሎች አስተባበሪዎችና ለዘርፉ ቀጥታ ተጠሪ የሆኑ ባለሙያዎችን ዕቅድ አዘጋጅቶ ይፈራረማል፣ ክትትልና ግምገማ በማድረግ አፈጻጸማቸውን ይመዝናል፣
- በተቋሙ የሚሰጡ ሥልጠናዎችን ለማን እንደሚሰጥ በበላይ ኃለፊ ታምኖበት ሲመራ በዘርፉ በኩል ታይቶ የሚያልፍ ሆኖ ልማት ዕቅድም ሥልጠናው በዕቅድ ስለመያዙ በጀት ስለመኖሩ ወይም በበጀት ስለመደገፉ እንዲረጋገጥ ያስደርጋል፡፡ ተገቢነቱም ከተረጋገጠ በግዥ፤ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ለሥልጠናው አስፈላጊውን ሁኔታ እንዲያመቻች ይመራል ለቢሮ ኃላፊም ሪፖርት ያደርጋል፡፣
- ዘርፉ የሰው ሃብት ልማት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የሥልጠናውን ውጤታማነት ቼክ ሊስት በማውጣት እንዲከታተል ያደርጋል፡፡ ውጤቱንም አይቶ ግብረ-መልስ እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡ ሪፖርት ተቀብሎ በተደራጀ መንገድ ለቢሮ ኃላፊ ያቀርባል፣
- ከምስሪያ ቤቱ ኃላፊ የሚሰጡ ሌሎች ተጨማሪ ተግባራትን ያከናውናል፡፡
የአሰተዳደርና ፋይናንስ ዘርፍ በስሩ የግዥና ንብረት አስተዳደር፣ የክፍያና ሂሳብ አስተዳደር፣ የዕቅድ፣ በጀት ዝግጅት፣ክትትልና ግምገማ እና የሰዉ ሀብት ልማት አስተዳደር ዳይሬክቶሬቶችን እንዲሁም የሰነ ምግባር መከታተያ፣የሥርዓተ ፆታ ጉዳይና የኤች አይ ቪ/ኤድስ ጉዳይ የስራ ክፍሎችን በማካተት የሚያስተባበር ዘርፍ ሆነው ተደራጅቷል፡: