• +251462204629
  • Hawassa , Ethiopia

የቻናል አንድ ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት

     ቻናል አንድ ፕሮግራሞች የመንግሥት የልማት ዉጥኖች ከግብ ለማድረስና ድህነትን ከሀገሪቱ ለማስወገድ የሚደረገዉን የመንግሥት የልማት እንቅስቃሴዎችን ጥረት በማገዝ ረገድ ከዉጭ ሀገር የሚገኘዉ ዕርዳታና ብድር የሚጫወተዉ ሚና በቀላሉ የሚገመት አይደለም፡፡ መንግሥት በዉጭ እርዳታና ብድር ሀብትን ለማገኘት በሀገሪቱ የተቀረፀዉን የመንግሥትን ፖሊስ ለማስፈፀም የሚያግዙ በግብርና፣ በትምህርት፣ በጤና፣በዉሃ፣ በመንገድ፣ በከተማ አስተዳደር፣ በሴቶች፣ በወጣቶች፣ በህፃናት እና በሌሎችም ዘርፍ የተለያዩ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶችና በማዘጋጀትና በመቅረጽ ከተለያዩ አለም አቀፍ ድርጅቶችና መንግሥታት ጋር የዉል ስምምነት በመፈራረም የተቀመጡ የዉጤት አመልካቾችን መነሻ በማድረግ የመደበኛ በጀት ክፍተት የሚሸፍን ተጨማሪ ሀብት በመገኘት የልማት ሥራዎችን በማፈጠን ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ ሁኔታ ከ1997 ዓ/ም ጀምሮ በድህነት ቀናሽ መሥሪያ ቤቶችና በሌሎችም መንግሥት መሥሪያ ቤቶች ከክልል እስከ ወረዳ/ቀበሌ ድረስ የሚተገበሩ የተለያዩ ፕሮግራሞችንና ፕሮጅክቶችን በመቅረፅ በርካታ ሀብት ተግኝቷል፣ እየተገኘም ይገኛል፡፡ ለአብነት የገጠር ልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም፣ የከተማ ልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም፣ የከተሞች መሠረተ ልማትና ማስፋፊያ ፕሮግራም፣ የከተሞች ተቋማዊና መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም፣ የመሬት ይዞታና ሰርትፍኬት አሰጣጥ ፕሮግራም፣ የትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም፣ የመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር ፕሮጅክት፣ የእንቨስተመንት ፕሮጀክት ፋይናንስንግ፣ የፍትሃዊ መሠረታዊ አገልግሎት ለሁሉ አቀፍ የዕድገት ተጠቃሚነት ፕሮግራም፣ የገጠርና የከተማ የመጠጥ ዉሃ ሃይጂንና ሳንቴሽን ፕሮግራም፣ የማህበረሰብ ትግበራ የገጠር የመጣጥ ዉሃ ፕሮግራም፣ የፋይናንስ ግልጽነትና ተጠያቂነት ፕሮጅክት እና ሌሎችም ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች ከክልሉ እስከ ወረዳ ድረስ የሚተገበሩ ናቸዉ፡፡ 

     አብዘኞዎቹ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች ሥራ ከጀመሩ ከ12 ዓመት በላይ ዕድሜ ያላቸዉ ሲሆኑ ጥቅቶቹ ከ7 ዓመት በላይ የቆዩ ናቸዉ፡፡ አንዱ ፕሮግራም በሌላ ፕሮግራም እየተተካ የሚሄድ ነወ፡፡ የፕሮግራሞች ዋና ዓላማቸዉም የመንግሥትን የልማት ሥራዎችን እንዲፋጣኑ በማድረግ ለህብረተሰቡ የሚሰጠዉ አገልግሎት አሰጣጥ ወቅታዊ፣ ጥራት ያለዉና ግልጽ እንዲሆን በማድረግ ተጠያቂነት የሰፈነበት የአሰራር ሥርዓት ማጠናከር ነዉ፡፡ የበጀት ምንጫቸዉም ዕርዳታ፣ ብድር፣ የመንግሥት መዋጮ እና የህብረተሰብ ተሳትፎ ናቸዉ፡፡ ከእነዚህም ምንጮች በፋይናንስ ቢሮ ለፕሮግራሞቹ ሀበት አስተዳደር ወደ ተከፈቱ ባንክ አካዉንቶች የሚፈሰዉ ለፕግራሞቹ ተጠቃሚዎች በሚደርሰዉ በቻናል አንድ የገንዘብ ፍሰት ነዉ፡፡ ቻናል አንድ በመባል የሚታወቀዉ የፈንድ ፍሰት ከለጋሽ አካላት የሚገኝ ገንዘብ በቀጥታ በፌዴራል ገንዘብ ሚኔስቴር ሂሳብ ዉስጥ ገብቶ ወደ ክልል ፋይናንስ ቢሮ በፕሮግራሞች ባንክ አካዉንት ገቢ ሆነዉ ከነዚህ ባንክ አካዉንቶች በሚቀርበዉ በጥሬ ገንዘብ ፍላጎት መርሃ ግብር መሠረት የጥሬ ገንዘብ ዝዉዉር እየተፈፀመ አፈጻጸሙ ድጋፍ፣ ክትትልና ግምገማ እየተደረገበት የሚከናወን ነዉ፡፡ ይህ የቻናል አንድ ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት በመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር ዘርፍ ሥር ከሚገኙ ዳይሬክቶሬቶች ዉስጥ አንዱ ሲሆን በዳይሬክቶሬቱ ሥር በርካታ ቡድኖች ይገኛሉ፡፡ እነርሱም የልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም ቡድን፣ የዋን ዋሽ ናሽናል ፕሮግራም ቡድን፣ የአጠቃለይ የትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም ቡድን፣ የከተሞች መሠረተ ልማትና ማስፋፊያ ፕሮግራም ቡድን፣ የኮ.ዋሽ ፕሮግራም ቡድን፣ የመሬት ይዞታና ሰርትፍኬት አሰጣጥ ፕሮግራም ቡድን፣ የመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር ቡድን፣ የከተማ አስተዳደር ልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም ቡድን እና የፋይናንስ ግልጽነትና ተጠያቂነት ፕሮግራም ቡድን ናቸዉ፡፡
የፕሮግራሙ ተጠቃሚዎችም ከክልል እስከ ወረዳ ድረስ የኢኮኖሚ ዘርፍ መንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ የማህበራዊ ዘርፍ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እና የአስተዳደርና አገልግሎት ዘርፍ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ናቸዉ፡፡