- በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማኀበረስብ ድርጅቶች በአዲሱ የፌዴራል የሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች አዋጅና መመሪያ እና በመንግስትና በሲቪል ማኀበረሰብ መመሪያ ይዘት መሰረት መስራታቸውን ይከታተላል፤ይቆጣጠራል፤ ይገመግማል፤ ከሲቪል ማኀበረስብ ድርጅቶች ኤጀንሲ የሚወጡ ህጎችን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን በስራ ላይ እንዲዉሉ ያደረጋል፣
- የሲቪል ማህበረብ ፕሮጀክቶችን በመምራት የሕዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ክልላዊ አዋጅ፤ ደንቦች፣ መመሪያዎችንና፣ መስፈርቶችን ያዘጋጃል፣ የአሰራር ስልቶችን ይቀይሳል፣ያዘጋጃል፤በስራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፤ አፈጻጸማቸውንም ይከታተላል፡፡
- የሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች የጋራ ምክክር መድረኮችን ያዘጋጃል፤ለምክክር መድረኩ ስትሪንግ ኮሚቴ ያቋቋማል፤
- የሲቪል ማኀበረስብ ድርጅቶች የሚተገበሩ የአዲስና ነባር ፕሮጀክቶች በማበልጸግ (Project appraisal)፤በሚተገበሩበት አከባቢ በሚታቀዱ ተግባራት ልክ ያለው ሀብት ተደልድሎ እንዲቀርብ ያደርጋል፤ተደልደሎ መቅረቡን ያረጋግጣል፤ያጸድቃል፤
- አዳዲስና ነባር የሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች የሚያቀርቡትን ፕሮጀክቶች ሰነድ በጀት የተገኘለት(secured) መሆኑን በማረጋገጥ የፕሮጀክት ስምምነት (Project agreement) ይፈራረማል፣
- ከፌዴራል ከሲቪል ማኀበረስብ ድርጅቶች አጄንሲም ሆነ ከክልሉ ፍትህ ቢሮ የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ምዝገባ ወስደው በክልሉ ስራ ለመጀመር ለሚፈልጉ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የስራ ስምሪት ፈቃድ ስምምነት/ Operational Agreement/ ለመስጠት መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎችን መርምሮ በማረጋገጥ ይፈራራማል፤ ወደ ስራ እንዲገቡ ምቹ ሁኔታዎችን እንዲፈጠር ያደርጋል፤
- ከሲቪል ማኀበረስብ ድርጅቶች የሚቀርቡ የፕሮጀክት ማሻሻያ እና የጊዜ ማራዘሚያ (Project amendment and extension) ጥያቄዎችን ተቀብሎ ተገቢነታቸውን መርምሮ ያረጋግጣል ፣ ያጸድቃል፣ ይከታተላል፣ይገመግማል፡፡
- የልማት ክፍተቶች ያለባቸውን አካባቢዎች ከስፍራ አንጻር በዓይነት(Gap Identification on Spatial and thematic areas) በጥናት እንዲለዩ በማድረግ፣ ሚዛናዊ የፕሮጀክቶች ስርጭት እንዲኖር ያመቻቻል ያደርጋል፤
- በልማት ከፍተት ልየታ (Gap Identification) ውጤት መሰረት የፕሮጀክት ሃሳቦች ተቀርጸውና ለልማት አጋሮች ቀርበው የሚደገፉበትን ስልት (project marketing) በስራ ላይ እንዲውል ምቹ ሁኔታዎች እዲመቻቹ ያደርጋል፣ ይከታተላል።
- የሲቪል ማህበረሰብ ፕሮጀከቶች የልማት ውጤት/ out come የሁኔታዎች ትንተና /situational analysis/ እንዲደረግ ማድረግ፤ የትንተና ውጤት ሰነዱንም ለባለድርሻ አካለት፣ ለምርምር ተቋማትና ለተጠቃሚ ተደራሽ እንዲደረግ ያደርጋል፣
- የሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች ፕሮጀክቶች የክትትልና ግምገማ ስርዓት ይዘረጋል፣ አሠራር ስርዓቱን ጠብቆ መሠራታቸውን በመስክ ይከታተላል፣ የዳሰሳ ጥናት ያካሂዳል በግኝቶች መሰረት የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፡
- በሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች የሚተገብሩ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም አንዲገመገም ባለድርሻ አካላቶችን በማስተባበር፤የአጋማሽና ማጠቃለያ ጊዜ ግምገማ ያደርጋል፤ ሪፖርትና ግብረ መልስ ያዘጋጃል፤ተደራሽ ያደርጋል፤
- በውጭ ኦዲተሮች የተሰራ የፕሮጀክት ብቻ የሆነ የኦዲት ግብረ መልሶችን ያካተተ የኦዲት ሪፖርት በመቀበል ለተግባራት አፈጻጸም አንጻር ተገቢነቱን መርምሮ ግብረ መልሱን ለሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቱ ያሰተላልፋል፤
- ለሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች ድጋፍና አገልግሎት መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች እንዲሟሉ በማድረግ፣ከቀረጥ ነጻ፣ የውጭ ዜጋ የመኖሪያ ፈቃድ፣ የባንክ አካውንትና ሌሎች አገልግሎቶች ድጋፍ እንዲሰጥ ያደርጋል፤
- በሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች በሚተገብሩ ፕሮጀክቶች አፈጻጻም ሂደት ላይ የሚፈጠሩ ግጭቶችና አለመግባባቶች በውይይት እንዲፈቱ ያደርጋል፤
- የተጠናቀቁ የሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች ፕሮጀክቶችን ንብረትና ውጤቶች ለሚመለከታቸው አካላት አሠራር ስራዓቱን ጠብቆ እንዲተላለፍና እንዲረካከብ ያደርጋል፤
- በክልሉ የሚተገበሩ ሲቪል ማኀበረሰብ ፕሮጀክቶች ዙሪያ ዝርዝር መረጃዎችን በማሰባሰብ፤ በማጠናቀርና በመተንተን ዓመታዊ የፕሮጀክት ፕሮፋይል አዘጋጅቶ ያሳትማል፤ለባድርሻ አካላትና ተጠቃሚዎች ተደራሽ ያደርጋል፤
- በሲቪል ማኀበረስብ ድርጅቶች ፕሮጀክቶች አሰተዳደር አንጻር በሚወጡ መመሪያዎች መሰረት የክትትልና ግምገማ ስራን በላቀ ደረጃ ለማከናወን የሚያስችል የስልጠናና የአቅም ግንባታ ስራዎችን ያከናውናል፤
- ከሲቪል ማህበረሰብ ፕሮጀክት መካከል የተሻለ የህብረተሰብ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ፕሮጀክቶችን በመለየት እውቅና እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡
- የሲቪል ማህበረሰብ ፕሮጀክቶች ክፍለ ኢኮኖሚያዊ ይዘት የሁነቶች ትንተና/situational Analysis/ ውጤቶችን መረጃ፤ ክፍለ ኢኮኖሚያዊ የሲቪክ ማህበራዊ ፕሮጀክቶች ስፍራዊ /Spatial distribution/ስርጭት የሚያሳይ መረጃን (Intervention map) አደራጅቶ ለተጠቃሚዎች እንዲደርስ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፤ ስርጭታቸውም በዚሁ እንዲቃኝ ተገቢው ድጋፍ ያደርጋል
- የሲቪል ድርጅቶች፣ፕሮጀክቶችን መረጃን በሶፍትዌር በመጠቀም በኮምፒውተር በማደራጀት፣ ተንትኖ ዓመታዊ የፕሮጀክት ፕሮፋይል እንዲዘጋጅ፤ ተደራሽ በማድረገ ፈጣንና ቀልጣፋ የአገልግሎት አቅርቦትን ለተጠቃሚ ተደራሽ እንዲደረግ ያደርጋል፤ ሲቪል ማሕበረሰብ ፕሮጀክቶች ያሰገኙት ውጤትና ፋይዳ ደሰሳ ጥናት ያካሄዳል
- የክልሉ ለሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች ከሊዝ ነጻ/ምደባ የሚሰጣቸውን የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በፋይናንስ ቢሮ ስም እንዲዘጋጅ ማድረግና የሊዝ ውል ስምምነት መፈራረም፣መሬቱ ለታለመለት አላማ መዋሉን ማረጋገጥ /መቆጣጠር፣ በየሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች የያዙትን ይዞታ የድርጅቱ ሰራ ሲጠናቀቅ/ሲዘጋ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በፋይናንስ ቢሮ ስም እንዲዞር ማድረግ፣
- በየአስተዳደር እርከኑ ለሚገኙ ሴክተር ባለሙያዎች የፕሮጀክት ክትትልና ግምገማና ሌሎች በሚዘጋጁ መመሪያዎችና ማኑዋሎች ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ይሰጣል፤
- በዘርፉ ለተሰማሩ ወይም መሰማራት ለሚፈልጉ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማሀበራት የስራ መረጃ፣ ሙያዊ ድጋፍና የምክር አገልግሎት ይሰጣል፤
- የዳይሬክቶሬቱን ዓመታዊ፣ የሩብ ዓመት፣ የግማሽ ዓመት፣ የዘጠኝ ዓመት ዕቅድና የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶችን ለቅርብ ኃላፊና ለቢሮ በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ያቀርባል፣
- ዳይሬክቶሬቱን በሚመለከቱ በተለያዩ ስብሰባዎች፣ሴሚናሮች ላይ በመገኘት የልምድ ልዉዉጦችንና ግንዛቤ በመቀመር በዳይሬክቶሬት ሥር የሚገኙ ባለሙያዎችን ዉጤታማ የሆነ ሥራ እንዲያከናወኑ ማድረግ፣የተገልጋዮችን እርካታ ደሰሳ ጥናት እንዲካሄድ በማድረግ የዳይሬክቶሬቱን አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት የሚሻሻልበት ሁኔታ ይቀይሳል፣
- በዳይሬክቶሬቱ የሰዉ ኃይል በመዋቅሩ መሠረት እንዲሟላ ያደርጋል፣
- በዳይሬክቴሩ የሚያስፈልጉ የሥራ ቁሳቁሶች እንዲሟላ ያደርጋል፣
- ለስራው ለማስፈፀም የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራቶችን ይፈጽማል፡፡