የሰነ-ምግባር መከታተያ ክፍል
- በተቋሙ ውስጥ ለሙስናና ብልሹ አሠራር ቀዳዳ የሚከፍቱ የአሠራር ችግሮችን በማጥናት አዳዲስ አሰራር ማንዋሎችና የመተዳደሪያ ኮዶፍ ኢቲክስ ያዘጋጃል፣የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን ይሰጣል፣ጥቆማዎችን ይመረምራል፣ እና ክትትል ያደረጋል፤
- በተቋሙ ለሙስናና ብልሹ አሠራር ቀዳዳ የሚከፍቱ የአሠራር ችግሮችን ለመለየት የሚያስችል ጥናቶችን ያካሂዳል ፤ይለያል፤
- በተቋሙ ውስጥ ለሙስና ለብልሹ አሰራር ክፍተት የሚፈጥሩ ጉዳዮችን ለመለየት የሚስችሉ የአሰራር ክፍተቶችን ሊያሟላ የሚችል ተቋማዊ ረቂቅ የስነ-ምግባርና የብልሹ አሰራር ማንዋልና ያዘጋጃል፤ለሃላፊው ያቀርባል፤
- ከስነ-ምግባር ጉድለትና ከሙስና ጋር በተያያዘ የጥቆማ የአቅራቢዎች ሚስጢራዊነት ሊያረጋግጥ የሚችል የአሰራር ስርዓት ያዘጋጃል፡፡
- የስነ-ምግባር ተግባራትን የሚያጎለብቱ አሰራሮችን ሊያሻሽሉ የሚችሉ ጉዳዮች ላይ በየወቅቱ ጥናት ያካሂዳል፤ ለሃላፊው ያቀርባል፤
- የተቋሙን ሰራተኞች የስነ ምግባር አስተሳሰባቸውን ሊያጎለብቱ የሚችሉ የስልጠና ሰነዶችን ያዘጋጃል፤ ስልጠና ይሰጣል፤
- በተቋሙ የስነ-ምግባር የአሰራር ማንዋልና የመተዳደሪያ ኮዶፍ ኢቲክስ ያዘጋጃል፤ ስልጠና ይሰጣል፣
- ሀገር አቀፍ የስነ-ምግባርና የጸረ-ሙስና ፖሊሲዎች፣ደንቦችና መመሪያዎች ዙሪያ ለተቋሙ ማህበረሰብ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን ይሰጣል፡፡
- በተቋሙ ውስጥ ሃብታቸውንና የገንዘብ ጥቅማቸውን እንዲያስመዘግቡ የህግ ግዴታ ለተጣለባቸው ሰራተኞችና ሃላፊዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመስጠት ሀብታቸውን በአግባቡ እንዲያስመዘግቡ ያደርጋል፤በአግባቡ ይመዘግባል፤
- የስነ-ምግባር ተግባራትን የሚያጎለብቱ ተሞክሮዎችን ይቀምራል፤ያስፋፋል፤ አሰራሮችን በየወቅቱ ያሻሽላል፤
- የተቋሙ የስነ-ምግባርና የጸረ-ሙስና የአሰራር ማንዋል፣ኮዶፍ ኢቲክስ እንዲሁም የሀገሪቱ የስነ-ምግባር የጸረ-ሙስና ህጎችና መመሪያዎች በተቋሙ ውስጥ መከበራቸውን ይከታተላል፡፡
- በክትትል ወቅት የተገኙ የአሰራር ክፍተቶች በመለየት የመፍትሄ ሃሳብ ለሃላፊው ያቀርባል፡፡
- በስነ-ምግባርና በጸረ-ሙስና ፖሊሲዎች፣ደንቦችና መመሪያዎች ዙሪያ የተሰጡ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች ያመጡትን ለውጥ ይከታተላል፣
- ሠራተኞች የሚያቀርቧቸውን የስነ-ምግባር ችግሮችና ማንኛውም ደንብና መመሪያ ጥሰት ጥቆማዎችን ተቀብሎ ምርመራ ያደርጋል፤የማስተካከያ እርምጃ በመለየት ለውሳኔ ሃላፊው ያሳውቃል፡፡
- በስነ-ምግባር ጉድለት ምክንያት በተከሰቱ ችግሮች ላይ የተወሰዱ ዕርምጃዎችን ይከታተላል፣ወቅታዊ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት በማዘጋጀት ለበላይ ሃላፊ ያቀርባል፡፡