1/ አገልግሎቱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፣
ሀ/ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የሚጠቀሙባቸዉ ተመሳሳይ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ማዕቀፍ
ግዢ እንዲሁም ክልላዊ የጋራ ጠቀሜታ ያላቸዉን ዕቃዎችና አገልግሎቶች ግዥ
ያከናዉናል፡፡
ለ/ ግምታቸዉ በቢሮዉ በመመሪያ ከሚወሰን የገንዘብ መጠን በላይ የሆናቸዉ በመንግሥት
መሥሪያ ቤቶች ኃላፊነት ሥር ያሉ ዕቃዎቸዎችና አገልግሎቶች በሽያጭ ወይም በሌላ ዘዳ
እንዱወገደ ዉሳኔ የተሰጠባቸዉን ንብረቶች ያስወግዲል፡፡
ሐ/ የዚህ ንዑስ አንቀጽ ተራ ፊዯል (ሀ) እን (ሇ) እንተጠበቀ ሆኖ፣ ሇማንኛዉም የመንግሥት
መሥሪያ ቤት እንዱሁም በመንግሥት የልማት ዴርጅቶች ጥያቄ ሲቀርብሇት በሚመሇከተዉ
አካል አቅርቦ ሲፈቀዴ፡-
፩) በወቅታዊ የገበያ መረጃ ላይ የተመሠረተ የሀገር ዉስጥ እና የዓሇም አቀፍ የግዥ
አገልግሎት ይሰጣል፣
፪) የግዥ አፈጻጸምን የሚመሇከት የምክርና የስልጠና አገልግሎት ይሰጣል፡፡
መ/ በዚህ ንዑስ አንቀጽ ተራ ፊዯል (ሐ) መሰረት ሇመንግስት የልማት ዴርጅቶች ሇሚሰጣቸዉ
አገልግሎቶች ተመጣጣኝ ዋጋ ያስከፍላል፡፡
ሠ/ የንብረት ባሇቤት ይሆናል፣ ዉል ይዋዋላል፣ በራሱ ስም ይከሳል እንዱሁም ይከሰሳል፡፡
ረ/ ዓላማዉን ሇማሳካት አስፈላጊ የሆኑ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናዉናል፡፡
፪) አገልግሎቱ በዚሁ ንዑስ አንቀጽ ፩ ተራ ፊዯል (ሀ) እና (ሇ) የተመሇከቱትን ስልጣንና
ተግባራት በሥራ ላይ ሲያዉል፡-
ሀ/ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የሚጠቀሙባቸዉን ተመሳሳይ ዕቃዎችን አገልግሎቶች
የአገር ዉስጥ ግዢ አጠናቆ የማዕቀፍ ስምምነት በመፈራረም የመንግሥት መስሪያ
ቤቶች እንዱያውቁት ያዯርጋል፡:
ሇ/ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የሚጠቀሙባቸዉን ተመሳሳይ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ዓሇም ዓቀፍ ግዢ እንዱሁም ክልላዊ የጋራ ጠቀሜታ ያላቸዉን ዕቃዎችና አገልግሎቶች ግዥ ሂዯት በማጠናቀቅ ሇተጠቃሚ አካላት እንዱዯርስ ያዯርጋል፡፡
ሐ/ ልዩ ሙያዊ ዕዉቀት በሚያስፈልጋቸዉ ጉዲዮች አግባብ ካላቸዉ መንግስታዊ ተቋማት ምክር መጠየቅና ማግኘት ይችላል፡፡
አቋም
አገልግሎቱ
፩) የሥራ አመራር ቦርዴ (ከዚህ በኋላ “ቦርደ” እየተባሇ የሚጠራ)፤
፪) በክልለ መንግሥት የሚሰየም አንዴ ዋና ዲይሬክተሩ እንዯ አስፈላጊነቱ ምክትል ዲይሩክተር እና ፣
፫) ሇስራዉ አስፈላጊ የሆኑ ሠራተኞች ይኖሩታል፡፡
የቦርደ አባላት
፩) ቦርደ ቁጥራቸዉ እንዯ አስፈላጊነቱ የመወሰን በመንግስት የሚሰየሙ ሰብሳቢዉን ጨምሮ ከ፭ እስከ ፯ የሚዯርሱ አባላት ይኖሩታል፡፡
፪) የአገልግሎቱ ዋና ዲይሩክተር የቦርደ አባልና ፀሐፊ ይሆናል፡