• +251462204629
  • Hawassa , Ethiopia

የመንግስት የልማት ድርጅቶች አሁን ካሉበት ሁኔታ በተሻለ መንቀሳቀስ የሚችሉበት አቅም ላይ መድረስ ይገባቸዋል ተባለ፡፡

ይህ የተባለው በክልሉ ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ቁጥጥር ባለስልጣን በBSC እቅድ ዝግጅት አተገባበር ዙሪያ ለባለድርሻ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ስልጠና እየተሰጠ ባለበት ወቅት ነው፡፡በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደቡብ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ የመንግስት የልማት ድርጅቶች የክልሉ መንግስት ከፍተኛ በጀት መድቦላቸው የልማት ተግባራትን የሚያከናውኑና የመንግስትን ገቢ በማሳደግ የሚያግዙ ቁልፍ ተቋማት ሲሆኑ በተለይም ፋይናንስ ቢሮ ለሚያከናውናቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት ከቢሮው ጋር ተቀናጅተው ሊሰሩ፣ ራሳቸውን በብቃት በማሳደግ ከዚህ የተሻለ መንቀሳቀስ ይገባቸዋል ብለዋል፡፡አቶ ተፈሪ አባተ ንግግራቸውን በመቀጠል እኚህ የልማት ድርጅቶች የተቋቋሙበትን ዓላማ ለማስፈፀም በደቡብ ክልል ብቻ ሳይወሰኑ ድንበር ዘለል ሆነው በሌሎችም የሀገሪቱ ክልሎች በመንቀሳቀስ ትርፍና ኪሳራቸውን በግልፅ በማሳወቅ የተጣለባቸውን ኃላፊነት ሊወጡ ይገባል ብለዋል፡፡አቶ ተፈሪ ባለድርሻ አካላት በዕቅድ አዘገጃጀትና አመራር የበቃ እውቀት ሊኖራቸው እንደሚገባ ገልፀው የመንግስት ልማት ድርጅቶች ባለስልጣን ያዘጋጀው ስልጠናም በተገቢው ትኩረት እንዲከናወን በማሳሰብ የስልጠናውን መጀመር አብስረዋል፡፡ለሚቀጥሉት ተከታታይ ቀናት በሚሰጠው በዚህ ስልጠና በደቡብ ክልል ምክር ቤት የፋይናንስ፣ በጀትና ኦዲት ቁጥጥር ቋሚ ኮሚቴ ዋናና ምክትል ሰብሳቢ፣ የክልሉ የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ኃላፊ፣ ከክልል ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ፣ ከደቡብ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት፣ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን፣ ከደቡብ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት እንዲሁም ከፋይናንስ ቢሮ ጥሪ የተደረገላቸው የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡በስልጠናው ላይ የአፈፃፀም ስራ አመራር ስርዓት፣ ሚዛናዊ የውጤት ተኮር እቅድ፣ የእቅድ አፈፃፀም ክትትልና ግምገማ እና የእቅድ አፈፃፀም ምዘና እውቅናና ሽልማት በሚሉ ርዕሶች ገለፃ ተደርጎ ተሳታፊዎችም ላነሱት ጥያቄ ምላሽ ተሰጥቶ ስልጠናው ተጠናቋል፡፡

0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *