የልማታዊ መንግስት አንድን ደሃ ሀገር በፍጥነት ወደበለፀገ አገር የመቀየር ብቃት እንዳለው ከነ ክፍተቱም ቢሆን በተግባር ያረጋገጠ ነው፡፡ በደሃ ሀገሮች በኢኮኖሚው በተመረጠ ሁኔታ ጣልቃ በመግባት ልማትን ለማፋጠንና ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ የመንግስት ድርሻ ከፍተኛ እንዲሆን ከሚያስገድዱ በርካታ ምክንቶች አንዱ ገበያውና የግል ባለሃብቱ የማይሸፍኗቸው ለልማትና ለፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማነቆ የሚሆኑ በርካታ የገበያ ጉድለቶች መኖራቸው ነው፡፡
በዓሇም ገበያ ሇመወዳደር ዕውቀት፣ ክህሎትና ልማታዊ አስተሳሰብ ያሇው ሰፊ አምራች ዜጋን መፍጠር፤ በዋጋና በጥራት ተወዳዳሪ የሆነ መሰረተ ልማት መዘርጋት፤ የምርት ስራዎችን ሇመምራት ብቃትና ተነሳሽነት ያሇው ባሇሃብትና ሙያተኛ ያስፈልጋል፡፡ በአጭሩ ሁሇቱን ማነቆዎች በተሟላ መልኩ ያስወገዱ መንግስታት ፈጣንና ከሞላ ጎደል ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የተረጋገጠበት ዕድገት ሲያረጋግጡና ሃገራቸውን ከድህነት አላቀው ከበሇፀጉት አገሮች ጎራ ጋር ሲቀላቀለ ይታያል፡፡ Read More…