• +251462204629
  • Hawassa , Ethiopia

የመንግስት ትሬዠሪ ዳይሬክቶሬት

የዳይሬክቶሬቱ ዝርዝር የሥራ ኃላፊነትና ተግባራት:-

  • ዳይሬክቶሬቱን ዓመታዊ፣ የሩብ ዓመት፣ የግማሽ ዓመት፣ የዘጠኝ ዓመት ዕቅድና የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶችን ለቅርብ ኃላፊና ለቢሮ በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ያቀርባል፣
  • በክልሉ ምክር ቤት የፀደቀዉን ዓመታዊ በጀት መነሻ በማድረግ በመደበኛና በካፒታል፣ በደመወዝና በሥራ ማስኬጃ በመለየት በክልል ባለበጀት መሥሪያ ቤቶችና በክልለ ተቋማት ሥር በሚገኙ የስራ ክፍሎች፣ በዞኖች፣ በልዩ ወረዳዎች፣ በወረዳዎች እና በከተማ አስተዳደር ስም የበጀት መረጃ ለይቶ በመያዝ ይቆጣጠራል፣
  • ለዓመቱ የተፈቀደዉን በጀት መነሻ በማድረግ ከፌዴራል የሚገኝ ድጎማ ገቢ፣ ከክልል ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች፣ ከከልል ተቋማት፣ ከዞኖች፣ ከልዩ ወረዳ፣ ከወረዳ እና ከከተማ አስተዳደር ለመሰብሳብ በዕቅድ የተያዘዉን መረጃ አደራጅቶ በመያዝ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣
  • ከሁሉም የአስተዳደር እርከኖች የጥሬ ገንዘብ ፍላጎት በመሰብሰብ ዓመታዊ የጥሬ ገንዘብ ፍላጎት መርሃ ግብር በማዘጋጀት ለፌዴራል ገንዘብ ሚኒስቴር ያቀርባል፣
  • ከክልሉ ለፌዴራል ገንዘብ ሚኒስቴር በቀረበዉ ጥሬ ገንዘብ ፍላጎት መርሃ ግብር መሠረት የድጎማ በጀት ወይም ገቢ በወቅቱ መላኩን ይከታተላል፣
  • የክልል ቢሮዎች የሚያቀርቡትን የክፍያ ጥያቄ በመቀበል ከተፈቀደላቸዉ በጀትና የጥሬ ገንዘብ ፍላጎት መርሃ ግብር መሠረት የቀረበ መሆኑን በማጣራት የባንክ ጣሪያ ይመሰርታል፣
  • የክልል ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች የተሰጣቸዉን የባንክ ጣሪያ መነሻ በማድረግ ከፍያ መፈፀማቸዉንና ከማዕካለዊ ግምጃ ቤት በጥሬ ገንዘብ መተካቱን ያረጋግጣል፣
  • ከሁሉም አስተዳደር እርከኖች ተንከበላይ የ3 ወራት የጥሬ ገንዘብ ፍላጎት መርሃ ግብር ተዘጋጅቶ እንዲቀርብ በማድረግ በቀረበዉ መርሃ ግብር መሠረት ይፈፅማል፣
  • በየወሩ ለዞኖች፣ ለልዩ ወረዳዎች፣ ለወረዳዎች እና ለከተማ አስተዳደሮች የቀረበዉን የጥሬ ገንዘብ ፋላጎት መርሃ ግብርና የተፈቀደላቸዉን በጀት መነሻ በማድረግ የባንክ ማዛዣ ደብደቤ በማዘጋጀት የጥሬ ገንዘብ ዝዉዉር ይፈጽማል፣
  • ለክልል ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች፣ ለክልል ተቋማት፣ ለዞኖች፣ ለልዩ ወረዳዎች፣ ለወረዳዎች እና ለከተማ አስተዳደሮች የደመወዝ ገንዘብ ሲተላለፍ የሲቪል ሠራተኞችና የሚሊተሪ የሠራተኞችና የመንግሥት የጡረታ መዋጮ ድርሻ ከሚተላለፈዉ ገንዘብ ቀንሶ በማስቀራት በየወሩ ለብሔራዊ ባንክ ያስተላልፋል፣
  • የመንግሥት ገንዘብ በታለመለት ዓላማ ላይ ዉጤታማ በሆነ መንገድ እንዲዉል ለማድረግ ዘመናዊ የመንግሥት የጥሬ ገንዘብ አስተዳደር ሥርዓት በየደረጃዉ ወጥነት ባለዉ መንገድ እንዲዘረጋ ያደርጋል፣
  • በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በሳጥን የሚያዝ የጥሬ ገንዘብ ጣሪያ በመወሰን በዉሳኔዉ መሠረት እንዲተገበር ያደርጋል፣
  • የክልሉ የተጠቃለለ ፈንድ አካዉንት ሂሳብ መቆጣጠርና ማስተዳደር፣
  • የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን የባንክ ሂሳቦችን መክፈት፣ መቆጣጠር፣ ማስተዳደር እና የማይቀሰቀሱ የባንክ ሂሳቦችን ይዘጋል፣
  • በአመታዊና በተንከበላይ የ3 ወር የጥሬ ገንዘብ ፋላጎት መርሃ ግብር መሠረት ይገኛል ተብሎ በዕቅድ የተያዘ ገንዘብ፣ የተከፈለዉ እና ከወጪ ቀሪ የገንዘብ ሚዛን የሚያሳይ የገቢና የወጪ መግለጫ አዘጋጅቶ በመገምገም የአፈፃፀሙ ሪፖርቱን ለሚመለከታቸዉ አካላት ያቀርባል፣
  • በክልል ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች ዜሮ ሚዛን የክፍያ ሥርዓትን በማሻሻል ዘመናዊ የጥሬ ገንዘብ ፍሰት ሥርዓት ይዘረጋል፣
  • በዞንና በወረዳ የሚተገበረዉን አንድ የፋይናንስ የጋራ አገልግሎት(ፑል) ክፍያ ሥርዓት በመገምገም የሚታዩ ክፍተቶችን በማረም ወቅቱ የሚፈልገዉን ቴክኖሎጂ በመጠቀም የአሰራር ሥርዓቱን ዘመናዊ እንዲሆን ያደርጋል፣
  • ከመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የፈሰስ ሂሳቦች በወቅቱ ወደ ማዕከላዊ ግምጃ ቤት ገቢ እንዲሆን ያደርጋል፣
  • በክፍያ አፈጻጸም ላይ ክፍተት ያለባቸዉን የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን በመለየት የድጋፍና የክትትል ሥራዎችን በማከናወን ግብረ መልስ ይሰጣል፣
  • የአቅም ግንባታ ክፍተቶችን በመለየት በክፍያ አፈጻጸም ዙሪያ የሚታዩ የአፈጻጸም ችግሮችን በመለየት የሥልጠና ሰነድ አዘጋጅቶ ሥልጠና ይሰጣል፣
  • በቢሮ በሚዘጋጁ የዉይይት መድረኮች ላይ በመገኘት በክፍያና በጥሬ ገንዘብ አስተዳደር ዙሪያ በሚነሳ ጥያቄዎች ላይ ማብራሪያ ይሰጣል፣
  • የጥሬ ገንዘብ አስተዳደርና የክፍያ አሰራር ሥርዓትን በተመለከተ የሚፈለጉ መረጃዎችን አደራጅቶ ለገንዘብ ሚኒስቴርና ለሌሎችም አካላት ያቀርባል፣
  • በሁሉም አስተዳደር እርከን በጥሬ ገንዘብ አስተዳደርና አጠቃቀም ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በጥናት በመለየት ችግሮቹን በዘላቂነት እንዲፈታ ያደርጋል፣
  • ከእንስፔክሽንና ከዉስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ጋር በማቀናጀት አለአግባብ የተከፈሉ ክፍያዎች ተመላሽ ሆነዉ ወደ ማዕከላዊ ግምጃ ቤት ገቢ እንዲሆን ያደርጋል፣
  • የመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች እና የአሰራር ማንዋሎች ሲዘጋጁ የጥሬ ገንዘብ አስተዳደርና የክፍያ አሰራር ሥርዓትን በተመለከተ አሰራር ሥርዓትን ዉጤታማ ሊያደርጉ የሚችሉ ሀሳቦችን ያቀርባል፣
  • የመንግሥት ገቢ የሚሰበሰብባቸዉ የገቢ ደረሰኞች በጥንቃቄ እንዲጠበቁ ክትትል ያደርጋል፣
    • የመንግሥት ገንዘብ ክፍያ የሚፈጸምባቸዉ የሂሳብ ሰነዶችና ቼኮች በአግባቡ እንዲጠበቁ ያደርጋል፣
  • ክፍያ የተፈጸመባቸዉ የክፍያ ሰነዶች በወቅቱ በተቀናጀ በፋይናንስ አስተዳደር መረጃ ቋት(IBEX) እንዲመዘገቡ ለሂሳብና ሪፖርት ማጠቃለያ ዳይሬክቶሬት በየዕለቱ ያስተላልፋል፣
  • በዳይሬክቶሬቱ የሰዉ ኃይል በመዋቅሩ መሠረት እንዲሟላ ያደርጋል፣
  • በዳይሬክቴሩ የሚያስፈልጉ የሥራ ቁሳቁሶች እንዲሟላ ያደርጋል፣
  • በቢሮ የዳይሬክቶሬቱ መዋቅር ሲዘጋጅ አስፈላጊዉን ግብዓቶችን በማቅረብ አብሮ ያዘጋጃል፣