የመንግስት ሂሳብ ማጠቃለያ ዳይሬክቶሬት
- ዳይሬክቶሬቱ ከዘርፉ ዓላማ በመነሰት የዳይሬክቶሬቱን ሥራዎች በማቀድ፣ በመምራትና በማስተባበር የመንግሥት ሂሳብ አያያዝ ሥረዓት በማስተገበር፣ በማገምገምና በማሻሻል የመንግሥት ሂሳቦች በወቅቱ እንዲቀርቡ፣ እንዲጠቃላሉ እና እንዲዘጉ በማድረግና በማስመርመር እንዲሁም የአቅም ግንባታ ሥራዎችን በመስጠት፣ በመከታተል እና በመደገፍ ዘመናዊ የመንግሥት ሂሳብ አያያዝና አገልግሎት አሰጣጥ እንዲኖር ያደርጋል፡፡
የመንግሥት ሂሳብ ማጠቃለያ ዳይሬክቶሬት ዝርዝር የሥራ ኃላፊነትና ተግባራት - አለም አቀፍ ይዘት ያለዉ የተቀናጀ ዘመናዊ የፋይናንስ መረጃ አያያዝ ሥርዓትን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እንዲዘረጋና እንዲተገበር ማስተባበር፣ መከታተል፣ መደጋገፍና ማስፈፀም፣
- የመንግሥት ሂሳብ አያያዝ ሥርዓት የተቀመጠዉን ስታንዳርዱን ተከትሎ እንዲፈፀም የአሰራር ሥርዓት ሊያሳዩ የሚችሉ ማንዋሎች እንዲዘጋጁ ማድረግ፣
- የመንግሥት ሂሳብ አሰራር ሥርዓት እንዲሻሻል የተለያዩ ጥናቶች እንዲካሄዱ በማድረግ በሚቀርቡ ጥናቶችን ላይ ቴክኒካዊ ግምገማዎችን በማካሄድ አሰራር ሥርዓቱን ወቅታዊ ያደርጋል፣
- የአገር አቀፍ ደረጃዎችን ልያሟሉ የሚችሉ የሂሳብ ሙያ መለኪያዎች(Accounting Standards) ተጠንቶ ሲቀርቡ ከበላይ ኃላፊዎች ጋር በማነጋገር በሥራ ላይ እንዲዉል ሲወሰን ለክልሉ ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች፣ ለዞኖች፣ ለልዩ ወረዳዎች፣ ለወረዳዎች እና ለከተማ አስተዳደሮች የተሸሻሉ ሰነዶች በማሰራጨት በሥራ ላይ መዋላቸዉን ይከታተላል፣
- የተቀናጀ የፋይናንስ አስተዳደር መረጃ ሥርዓት የሚመራባቸዉ መመሪያዎችና የአሰራር ማንዋሎችን ተዘጋጅቶ እንዲተገበሩ ማድረግና አፈጻጸማቸዉን ይከታተላል፣
- በፌዴራል እንዲሁም በሌሎች ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ደረጃ የተቀመሩ የመንግሥት ሂሳብ አያያዝ ምርጥ ተሞክሮ ዘዴዎችን በመዉሰድ ወደ ተግባር እንዲለወጥ ያደርጋል፣
- በመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር ሥር የሚገኙ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የሥልጠና የዳሰሳ ጥናት እንዲካሄድ በማድረግ በጥናቱ ዉጤት መሠረት የሥልጠና ሰነድ ማዘጋጀት፣
- ከመንግሥት ሂሳብ አያያዝ ሥራዎች ጋር በተያያዘ ለሚዘጋጁ የመሥሪያ ቤቱ አዋጅ፣ ደንብ እና መመሪያዎች በጥናት የተደገፈ ግብዓቶችን መስጠትና ሲፀድቅም በሥራ ላይ ማዋሉን ይከታተላል፣
- ከትሬዥሪ ዳይሬክቶሬት የሚቀርቡ ሰነዶችን መሠረት በማድረግ የየቀኑን የወጪና ገቢ ሂሳቦች እንቅስቃሴ መመዝገብ፣ ማዋራረስ፣ ወቅታዊ የሆነዉን የሂሳብ መረጃዎችን መነሻ በማድረግ ወቅታዊ የሂሳብ ሪፖርቶችና በማዘጋጀት ለሚመለከታቸዉ አካላት ሁሉ ተደራሽ ማድረግ፣
- የሂሳብ እንቅስቃሴዎች በተፈቀደላቸዉ የሂሳብ መደቦች አቅጣጫዎችን ጠብቆ እንዲመዘገቡ ያደርጋል
- ሂሳቦች በየወሩ በተፈቀደላቸዉ ሂሳብ አቅጣጫዎች መሠረት ሚዛናቸዉ በትክክል እንዲታረቁ ያደርጋል፣
- የክልል ባለበጀት መሥሪያ ቤቶችና ተቋማት ጥሬ ገንዘብ ያልሆኑ (Non Cash Transaction) የፈሰስ ሂሳቦች ተቀብሎ ይመዘግባል፣
- የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ወርሃዊ የሂሳብ ሪፖርቶች(የገቢ፣ የወጪ፣ የተሰብሳቢ፣ የተከፋይ፣ የዝዉዉር እና የሂሳብ ማመዛዘኛ) በተቀናጀዉ ዘመናዊ የፋይናስ መረጃ ሥርዓት በትክክል መመዝገባቸዉንና መታረቃቸዉን በማረጋገጥ ግብረ መልስ ይሰጣል፣
- የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የባንክ ማስታረቂያና የጥሬ ገንዘብ ቆጠራ ሰርተፍኬት በትክክል እንዲዘጋጅና ለዳይሬክቶሬቱ እንዲቀርብ ያደርጋል፣
- የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የተከፋይና የተሰብሳቢ ሂሳቦች በዕድሜ ዘመን(Aging Analisis) ለይቶዉ መዝግቦ እንዲያቀርቡና የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ በማድረግ ሚዛናቸዉ እንዲቀንስ ያደርጋል፣
- የመንግሥት ገቢና ወጪ፣ የተፈቀደ በጀትና ወጪ፣ የሀብትና የዕዳ ዓመታዊ መግለጫዎች በማዘጋጀት ለሚመለከታቸዉ አካላት ያቀርባል፣
- የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ያቀረቡት የበጀት፣ የገቢ፣ የወጪ፣ የተሰብሳቢ፣ የተከፋይ እና የዝዉዉር ሂሳቦችን ወቅታዊነት በማረጋገጥ ከተፈቀዱ በጀት ምንጮች ጋር የሚታረቅ መሆኑን ያረጋግጣል፣
- የተሰብሳቢና የተከፋይ ሂሳቦች መሰብሰብና መክፈል የማይችሉ መሆናቸዉን በመለየት ከመዝገብ እንዲሰረዝ በደንቡና በመመሪያ መሠረት መረጃ እንዲደራጅ በማድረግ ለዉስጥና ለወጪ ኦዲተሮች እንዲቀርብ ያደርጋል፣
- የተጠቃለሉ የሂሳብ ሪፖርቶችን በመዝጋት በሃርድና በሶፍት ኮፒ እንዲደራጅ በማድረግ ለዉስጥና ለዉጭ ኦዲተሮች በማቅረብ እንዲመረመር ያደርጋል፣
- የወስጥና የዉጭ ኦዲተሮች ለሚጠይቁት ጥያቁዎች ማብራሪያ ይሰጣል፣
- በኦዲት ግኝቶች ላይ የኦዲት ማጠቃለያ የመዉጫ ስብሰባ(Exit Conference) የመሥሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊዎች በተገኙበት ለሚነሱ ለኦዲት ጉዳዮች ምላሽ ይሰጣል፣
- ኦዲት የተደረጉና የተጠቃለለ የመንግሥት ሂሳብ ሪፖርት ለዜጎች፣ ለልማት አጋሮች እና ለልዩ ልዩ ተጠቃሚ አካላት እንዲጠቀሙበትና እንዲያወቁት ያደርጋል
- በተገኙት ኦዲት ግኝቶች ላይ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ በማድረግ ግብረ መልሱን ለሚመለከታዉ አካላት ያቀርባል፣
- በየበጀት ዓመቱ ከመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በሚሰጡ ኦዲት አስተያየቶች የማስተካከያ እርምጃ ለመዉሰድ የሚያስችሉ የድርግት መርሃ ግብር ማቅረቢያ ቼክሊስት በማዘጋጀት በመከታተል በኦዲት ግኝቶች ላይ የማስተካከያ እርምጃ መዉሰዳቸዉን ያረጋግጣል፣
- ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸዉን የክልል ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች፣ ዞኖች፣ ልዩ ወረዳዎች፣ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች በመለየት፣ የተለዩ ችግሮች ማስተካከል የሚያስችሉ ቼክ ሊስት በማዘጋጀት ድጋፍና ክትትል ማድረግ፣ አፈጻጸሙን መከታተልና ግብረ መልስ ይሰጣል፣
- በክልል ባለበጀት መ/ቤቶች፣ በዞኖች፣ በልዩ ወረዳዎች፣ በወረዳዎች እና በከተማ አስተዳደሮች ዉስጥ ለረጅም ጊዜ ሲንከባለሉ የመጡ ያልተወራረዱና ሊወራረዱ የማይችሉ ተሰብሳቢና ተከፋይ ሂሳቦች በዕድሜ ዘመን መረጃዉ ተዘጋጅቶ በአግባቡ መያዛቸዉን ያረጋግጣል፤
- ለመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እና ተቋማት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በመንግሥት ሂሳብ አያያዝ ሥርዓት ላይ የአቅም ግንባታ ሥልጠናና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናዎችና በመስጠት የሥልጠና ፋይዳዉን ይፈትሻል፣የስልጣናውን ዉጤታማነት ዳሰሳ ጥናት ያደርጋል፤
- ወርሃዊ፣ የሩብ ዓመት፣ የስድስት ወር፣ የዘጠኝ ወር እና ዓመታዊ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በማዘጋጀት ለሚመለከታቸዉ አካላት በመስጠት በሚሰጠዉ ግብረ መልስ መሠረት የማስተካከያ እርምጃ መዉሰድና ስለመወሰዱ ይከታተላል፤
- የዳይሬክቶሬቱን ዓላማ ለማሳካት የሚያስፈልገዉ የሰዉ ኃይልና የሥራ ግብዓቶች እንዲሟላ ያደርጋል
- በዳይሬክቶሬቱ ሥራ ለተመደቡ ባለሙያዎች እንደየደረጃቸዉ ዝርዝር የሥራ ድርሻ በመስጠት በቅርበት በመከታተልና በመገምገም አፈጻጸማቸዉን በመሙላት ግብረ መልስ ይሰጣል፣
- የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች ክፍተት በመለየት ባለሙያዎች ሥልጠናና ግንዛቤ እንዲያገኙ ያደርጋል፣
- ዳይሬክቶሬቱን በሚመለከቱ በተለያዩ ስብሰባዎች፣ሴሚናሮች ላይ በመገኘት የልምድ ልዉዉጦችንና ግንዛቤ በመቀመር በዳይሬክቶሬት ሥር የሚገኙ ባለሙያዎችን ዉጤታማ የሆነ ሥራ እንዲያከናወኑ ማድረግ፣የተገልጋዮችን እርካታ ደሰሳ ጥናት እንዲካሄድ በማድረግ የዳይሬክቶሬቱን አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት የሚሻሻልበት ሁኔታ ይቀይሳል፣
- በቢሮ ዳይሬክቶሬቱን በሚመለከት የመዋቅር ጥናት የሚደረግ ከሆነ አስፈላጊዉን ግብዓቶችን በማቅረብ ባለሙያዎች እንዲሰተፉ ያደርጋል፣
- በየዕለቱ በተቀናጀዉ በመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር የመረጃ ቋት ሂሳቦችን ለመመዝገብ ከትሬዠሪ ዳይሬክቶሬት የሂሳብ ሰነዶችን ዝርዝር ይረከባል
- በቀረቡት የሂሳብ ሰነዶች መሠረት የሂሳቦች ጥራት በመጠበቅ ምዝገባ ማካሄድ፣
- ሂሳቦች ከተመዘገቡ በኃለ የሂሳብ ሰነዶችን በመሄ 42 በዝርዝር በመመዝገብ ለሰነድ ያዥ ያስረክባል፣
- የሂሳብ ሰነዶች በሰነድ ክፍል መረጃ ፈላጊዎች በቀላሉ መገኘት በሚችሉበት ሁኔታ በየዓመቱ በየወሩ እና በቀን ተለይቶ እንዲደራጁ ያደርጋል፣
- ለሰነድ አያያዝና አጠባበቅ የሚያስፈልጉ የተለያዩ ቁሳቁሶች እንዲሟሉ ያደርጋል፣
- የሰነድ አያያዝና አጠባበቅ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እንዲታገዝ ያደርጋል፣
- ኦዲት ተደርጎ ከ10 ዓመት በላይ ከቆዩ ከሂሳብ ሰነዶች በፍርድ ቤት የሚፈለጉትን በመለየት እንዲወገዱ ለሚመለከታቸዉ አካላት ያቀርባል፡፡