• +251462204629
 • Hawassa , Ethiopia

የመንግስታት ትብብር ዳይሬክቶሬት

 • የክልሉ መንግስት የብድርና እርዳታ ስምምነቶችን ይፈራረማል፣ ያስተዳደራል፤
 • ከመንግስታትና ዓለም አቀፍ ረጂ ድርጅቶች ሀብት ያፈላልጋል፣
 • በመንግስታት ትብብርና ድጋፍ የሚከናወኑ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች ከመንግስት የልማት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ጋር የተጣጣሙ መሆናቸውን ያረጋግጣል፤
 • በመንግስታት ትብብርና ድጋፍ ለሚካሄዱ ፕሮግራሞች የሚመጣውን ገንዘብ ለፈፃሚ የክልል ማዕከላት፣ ዞኖችና ወረዳዎች እንዲተላለፍ ያደርጋል፤ መድረሱን ያረጋግጣል፤
 • በመንግስታት ትብብርና ድጋፍ የሚከናወኑ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶችን ፕሮፋይል ያዘጋጃል፤ ተደራሽ ያደርጋል፤
 • የመንግስታት ትብብር ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች እንዲሁም የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ዕርዳታና ብድር ፕሮግራሞች/ፕሮጀክቶች ዓመታዊ እቅድና በጀት (Annual work plan) ያዘጋጃል፤ያስፀድቃል፤ የፀደቀውንም በጀት ያስተላልፋል፤
 • የመንግስታት ትብብር፣ የእርዳታና ብድር ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶችን የየሩብ ዓመት ፊዚካልና ፋይናንሺያል አፈፃፀም ሪፖርት ከፈፃሚ አካላት ያሰባስባል፤ ያጠናቅራል፤ ለረጂ ድርጅቶች ያስተላልፋል፤
 • በመንግስታት ትብብር፣ የእርዳታና ብድር የሚከናወኑ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶችን የዕቅድ አፈፃፀም በመስክ ክትትልና ግምገማ ያደርጋል፤
 • የዕርዳታና ብድር ፕሮግራሞች የስድስት ወርና ዓመታዊ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ (Review Meeting) ያዘጋጃል፤ ሪፖርት ያቀርባል፤
 • በየአስተዳደር እርከኑ ለሚገኙ ሴክተር ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ይሰጣል፤
 • የዳይሬክቶሬቱን ዓመታዊ፣ የሩብ ዓመት፣ የግማሽ ዓመት፣ የዘጠኝ ዓመት ዕቅድና የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶችን ለቅርብ ኃላፊና ለቢሮ በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ያቀርባል፣
 • ዳይሬክቶሬቱን በሚመለከቱ በተለያዩ ስብሰባዎች፣ሴሚናሮች ላይ በመገኘት የልምድ ልዉዉጦችንና ግንዛቤ በመቀመር በዳይሬክቶሬት ሥር የሚገኙ ባለሙያዎችን ዉጤታማ የሆነ ሥራ እንዲያከናወኑ ማድረግ፣የተገልጋዮችን እርካታ ደሰሳ ጥናት እንዲካሄድ በማድረግ የዳይሬክቶሬቱን አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት የሚሻሻልበት ሁኔታ ይቀይሳል፣
 • በዳይሬክቶሬቱ የሰዉ ኃይል በመዋቅሩ መሠረት እንዲሟላ ያደርጋል፣
 • በዳይሬክቴሩ የሚያስፈልጉ የሥራ ቁሳቁሶች እንዲሟላ ያደርጋል፣
 • ስራውን ለማስፈፀም የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራቶችን ይፈጽማል፡፡