ኤች አይቪ/ኤድስ ጉዳዮች መከታተያ ክፍል
- ኤች አይ ቪ/ኤድስ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችሉ፣የሕግ ማእቀፎችን በማዘጋጀት ስልጠና ይስጣል፣ ረቂቅ ፖሊሲ፣አዋጅ፣ ደንብ እና መመሪያ ያዘጋጃል፤
- ፖሊሲንና የሕግ ማእቀፎችን ለመከለስና የአሠራር ስልቶችን ለማሻሻል የሚረዱ በጥናት ላይ የተመሠረቱ ሙያዊ ሀሳቦችን ያመነጫል፣ ተግባራዊ ያደርጋል፣ አፈፃፀማቸውን ይከታተላል፣
- በፖሊሲውና በሕግ ማዕቀፎች ላይ የአድቮኬሲ/የማሳመን/ ሥራዎችን ይሠራል፣ተፈፃሚነታቸውን ይከታተላል፣
- በቡድኑ የሚገኙ ባለሙያዎች አቅም እንዲገነባና በቂ ክህሎት እንዲኖራቸው የዳሰሳ ጥናት ያካሂዳል፣
• የተለያዩ የአቅም ግንባታ ቢጋር (TOR) እና የመግባቢያ ሰነድ (MOU) በማዘጋጀት ለኃላፊው ያቀርባል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊነቱን ይከታተላል፣ - የአቅም ግንባታና ሜይንስትሪሚንግ ሥራ ውጤታማ እንዲሆን የአሰልጣኞች ስልጠና ያዘጋጃል፣ ስልጠና ይሰጣል፣
- ኤች አይ ቪ/ኤድስን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አኳያ አዳዲስ ሃሳቦችን ያመነጫል፣ ለኃላፊው ያቀርባል፣ሲፈቀድም ለተግባራዊነቱ ይሰራል፣
- ኤች አይ ቪ/ኤድስን የመከላከልና የመቆጣጠር እንዲሁም የድጋፍና እንክብካቤ ሥራዎችን ለማከናወን የሚያግዙ ፕሮጀክቶችን እና ፕሮፖዛሎች ያዘጋጃል፣ ያስገመግማል፣ ተቀባይነት ሲያገኙ በሥራ ላይ ያውላል ተግባራዊነታቸውን ይከታተላል፣
- በኤች አይ ቪ/ኤድስ ዙሪያ በሚካሄዱ አለም አቀፍም ሆነ ሀገራዊ ጉባኤዎች፣ አውደ ጥናቶች፣ ሴሚናሮች፣ ሲምፖዚሞች ላይ በመሳተፍ የተገኙትን ልምዶች እና ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር ለኃላፊው ያቀርባል ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፣
- በየመስሪያ ቤቱ በሚዘጋጁ ደንቦች፣ መመሪያዎች ፕሮግራሞችና እቅዶች ላይ የኤች አይ ቪ/ኤድስ ጉዳይ መካተቱን ይከታተላል፣ እንዲካተቱም ያደርጋል፡፡
- በኤች አይ ቪ/ኤድስ ዙርያ ከሚንቀሳቀሱ አጋር አካላት ጋር በዘላቂነት በትብብር ለመስራት መድረኮችን አዘጋጅቶ ለኃላፊው ያቀርባል፣ሲፈቀድም ተግባራዊነታቸውን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ አፈፃፀሙን ሪፖርት ያደርጋል፣
- የፀረ ኤች አይ ቪ/ኤድስ እንቅስቃሴን የበለጠ ውጤታማ ማድረግ የሚያስችሉ አዳዲስ አሠራሮች ሥራ ላይ ያውላል፣ አፈፃፀማቸውን ይገመግማል፣ ተግባራዊነታቸውን ይከታተላል፣
- በኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ የሚደረጉ የጥናት የምርምርና እና የሙከራ ውጤቶች ላይ በመመርኮዝ የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራ ውጤታማ እንዲሆን ያደርጋል፣
- በኤች አይ ቪ/ኤድስ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚረዱ መረጃዎች አግባብነታቸውን በመገምገምና በመመዘን በመሥሪያ ቤቱ ለሚገኙ ሠራተኞች የሚደርሱበትን ስልቶች ይነድፋል ለተግባራዊነታቸውም ከቡድን መሪው ጋር በመሆን ይሰራል፣
- ኤች አይ ቪ/ኤድስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከሚንቀሳቀሱ የዘርፍ አቻ መስሪያ ቤቶች ጋር የትብብር ፎረም ዝግጅት ላይ አንድ አካል በመሆን የተለያዩ ግብዓቶችን በማቅረብ ያመቻቻል፣ ይሳተፋል፣ የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችንና ልምዶችን በመቀመር ያስፋፋል፣ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
- 0.5% ከመንግስት ሠራተኛው የሚመጣዉ ድጋፍና እንክብካበ ሀብት ለታለመለት ዓላማ መዋሉን ይከታትላል፣በኦዲትም እንዲረጋገጥ ያደረጋል፤
- ኤች አይ ቪ በደማቸው ለሚገኝባቸው ሠራተኞች፣ በኤች አይ ቪ/ኤድስ ምክንያት ወላጆቻቸውን ላጡ ህፃናትና ወጣቶች ድጋፍና ክብካቤ እንዲሁም ራሳቸውን የሚችሉበት የገቢ ማስገኛ መንገዶችን ስልት ይቀይሳል፣ይተገብራል፣ይከታተላል፣
- ኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠርን አስመልክቶ ለሚመለከታቸው አካላት ሙያዊ ድጋፍ ይሰጣል፣ ክትትል ያደርጋል፣ ወቅታዊ ግብረ መልስ ይሰጣል፣
- የኤች አይ ቪ/ኤድስ ፈንድ የሚቋቋምበትንና ፈንድ የሚገኝበትን ሁኔታ ያመቻቻል በአግባቡ ሥራ ላይ ያውላል፣ ይከታተላል፣ አፈፃፀሙን በመገምገም ለኃላፊው ያቀርባል፡፡