ኢኮቴ ዳይሬክቶሬት
ቴክኖሎጂ ለአንድ ሃገር ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኀበራዊ ዕድገት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከምንም በላይ መሆኑን ዛሬ ላይ የስልጣኔ ጫፍ የደረሱ ፣ የበለፀጉና የዓለማችን ሃያላን ተብለው የሚጠሩ አገሮች ምሥክሮች ናቸው፡፡ ይህም በመሆኑ መንግሥት የሃገራችን ሕዝብ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንዲሆንና የቴክኖሎጂው ሽግግር ከጫፍ እንዲደርስ ተግቶ በመሥራቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ቀላል የማይባል የሃገራችን ሕዝብ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ መሆን ችሏል፡፡
ምን ይሰራል
- የፋይናንስ ሲስተም ሶፍተዌሮችን ያስተዳደራል
- የለሙ የፋይናንስ ሲስተሞች/ሲስተም ሶፍትዌሮች/
- IBEX (Integrated Budget and Expenditure)፣
- IFMIS (Integrated Financial Management Information System)
- DEVInfo /Development Information System/
- Payroll System ፣
- Inventory System ፣
- Form Tracking System፣
- Personnel Management System
- Suppliers Management System
- የለሙ የፋይናንስ ሲስተሞች/ሲስተም ሶፍትዌሮች/
- የመረጃ መረብ /Network/ ይዘረጋል፣ ያስተዳደራል
- በቢሮው/ በመምሪያው/ በጽ/ቤቱ ውስጥ ያለውን ኔትወርክ
- IBEX and IFMIS VPN /Virtual Private Network/ (Woredanet)
- ድረ-ገፅ ያለማል፣ ያሻሽላል፣ ያስተዳድራል፣ የቢሮውን አስፈላጊና ወቅታዊ መረጃዎች ተደራሽ የደርጋል፣
- በፋይናንስ ሲስተም ሶፍተዌሮች ላይ ሥልጠና ይሰጣል፣
- የኢኮቴ መሣሪያዎች ጥገና ያደርጋል፣
- በፋይናንስ ሲስተም ሶፍተዌሮች ላይ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል
- የኢኮቴ መሣሪያዎች የግዥ ዝርዝር መሥፈርት (Specification ) ያዘጋጃል፣ የዕቃ አቅረቢው ሰነድ በተዘጋጀው Specification መሠረት መሆኑን ያጣራል፣ ያሸናፊ ድርጅት ያቀረበውን ዕቃ የቴክኒክ ምርመራ በማድረግ ያረጋግጣል፣
- በየበጀት ዓመቱ መጨረሻ ሂሳብ አዘጋግ ላይ በመሳተፍ ከዳታቤዝ አንፃር ሙያዊ ድጋፍ ይሰጣል
ለምን ይሰራል
- የሴክተሩ ተገልጋዮችና ባለድርሻ አካላት ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኙ ለማስቻል፣
- የሴክተሩን መረጃ ሥርዓት ደህንነት የተጠበቀ ለማድረግ፣
- በሴክተሩ የሚሰሩ ሥራዎችን በቴክኖሎጂ የተደገፉ ለማድረግ፣
- በፋይናንስ ሲስተም ሶፍተዌሮች ላይ የሰለጠነ ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት፣
- የሴክተሩን አስፈላጊና ወቅታዊ መረጃዎች ተደራሽ ለማድረግ፣
- ከፋይናንስ ሲስተም ሶፍተዌሮች የሚወጡ ሪፖርቶች ጥራትና ደረጃቸውን እንዲሁም ወቅታዊነታቸውን ጠብቀው እንዲዘጋጁ ለማስቻል፤
- በሴክተሩ ውስጥ በአገልግሎት ላይ ያሉ የICT መሣሪያዎች ወቅታዊ የሶፍትዌርና ሃርድዌር ጥገናና ፍተሻ ተደርጎላቸው የአገልግሎት ጊዜአቸውን ዘላቂና አስተማማኝ ለማድረግ፣
- በፋ/ኢ/ል/ ሴክተር የሚገዙ የICT መሣሪያዎች ደረጃቸውን የጠበቁና ጥራት ያላቸው እንዲሆኑ ለማስቻል፣