• +251462204629
  • Hawassa , Ethiopia

በልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም -4 እና በUIIDP ለተካተቱ አዳዲስ ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ

በዕለቱ የተሰጠው ስልጠና በክልሉ ፋይናነስ ቢሮ በልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም-4፣ በ UIIDP ማስተባሪያ ዳይሬክቶሬት ከቢሮው ኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽና ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባር የተዘጋጀ ነው፡፡
“በሁለት ዙር የተሰጠው ስልጠና ዓላማው ምንድን ነው?’ ብለን የጠየቅናቸው የስልጠናው አስተባባሪና የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ በላቸው ከበደ፡- “ስልጠናው የተዘጋጀበት ዋነኛ ዓላማ ወደ ልማታዊ ሴፍቲኔት እና UIIDP የተካተቱ ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደር ባለሙያዎችን የፋይናንስ አስተዳደር ስርዓቱ ምን እንደሚመስል ማስተዋወቅና ስለ ዘመናዊ የሂሳብ መተግበሪያ ዘዴ IBEX በተመለከተ በፕሮጀክቱ ለሚሳተፉ ባለሙያዎች ግንዛቤ መፍጠርና አቅማቸውን ማጎልበት ነው ብለዋል፡፡
አቶ በላቸው ንግግራቸውን በመቀጠል በስልጠናው ትኩረት የተደረገባቸው ይዘቶች በልማታዊ ሴፍቲኔትም ሆነ በUIIDP
ፕሮግራሞች በአገልግሎት ላይ የሚውሉ የፋይናንስ አስተዳደር ስርዓቶችና በIBEX ፋይናንስ ሞጁል አተገባበሮች ላይ ትኩረት ማድረግና የፋይናንስ አሰራር ህግን ተከትሎ ተግባራትን ማከናወን የሚሉ ይዘቶች በገለፃ፣ በውይይትና በጥያቄ መልስ ተደግፈው ለሰልጣኞች ይቀርባሉ ሲሉ አክለዋል፡፡
በስልጠናው የፋይናንስ አስተዳደር ስርዓት፣ የ IBEX ፋይናንሺያል ሞጁል ምንነት፣ አሰራር ቅደም ተከተሎችና አጠቃቀም በሚሉ ርዕሶች ዙሪያ ከቢሮው ባለሙያዎችና ተጋባዥ አሰልጣኞች ገለፃ ተደርጓል፡፡
በመጨረሻም በቀረቡ ርዕሶች ላይ ግልፅ ያልሆኑ ፅንሰሃሳቦችን በሚመለከት ገንቢ ውይይት የተደረገ ሲሆን፤ አሰልጣኝ ባለሙያዎች ከሰልጣኞች ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል፡፡

0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *