በክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ዉስጥ ከሚገኙ ዘርፎች አንዱ የመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር ዘርፍ ነዉ፡፡ መንግሥት ከተለያዩ የገቢ ምንጮች በገንዘብ ወይም በዓይነት የሚሰበሰብ ሀብት ለመንግሥት መደበኛና ካፒታል ሥራዎች ለሚያደረገዉ እንቅስቃሴ ወጪዎችን መሸፈንን፣ ማስተዳደር እና መቆጣጠርን አካቶ የሚመራ የሥራ ዘርፍ ነዉ፣ ከክልል እስከ ወረዳ/ቀበሌ ድረስ የመንግሥት ሀብት የሚመረባቸዉ የመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር የህግ ማዕቀፎችን በማዘጋጀትና በማፀደቅ ለክልል ባለበጀት መሥሪያ ቤቶችና ለአስተዳደር እርከኖች በማሰራጨት ሥራ ላይ እንዲዉል ከማድረግም አንፃር ተግባራትን የሚያከናወን ነዉ፡፡ የተፈቀደዉን በጀት፣ የተላለፈዉን ጥሬ ገንዘብ፣ የተከፈለዉን ክፍያ፣ በሥራ ላይ የዋለዉን ሀብት፣ የሀብትና የዕዳ፣ የገቢና የወጪ ፋይናንሻል ሪፖርቶችና መገለጫዎችን በማዘጋጀት ለሚመለከታቸዉ አካላት በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ዉስጥ ተደራሽ በማድረግ አፈጻጸሙን በዉስጥና በዉጭ ኦዲተሮች እንዲመረመር ያደርጋል፡፡ በተገኙት ኦዲት ግኝቶችም ላይ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ በማድረግ ግብረ መልስ ይሰጠል፡፡ በዘርፉ የተሟላ የሰዉ ኃይል እንዲሟላ በማድረግ የዘርፉ ባለሙያዎችንና የአመራር አካላት የክህሎት ክፍተት በመለየት የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን በማዘጋጀት የዘርፉ ሥራዎች ዉጤታማ እንዲሆኑ ከማድረግ አንፃርም ሚናዉ ከፍተኛ ነዉ፡፡
በአዋጁ ለዘርፉ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት ለመወጣት በስሩ ከክልል እስከ ወረዳ ድረስ በተደራጁት ዳይሬክቶሬቶቹ አማካይነት ክልላዊና የየአሰተዳደር እርከኑን ዘመናዊ የበጀት አስተዳደር፣ የሂሳብ አያያዝ፣ በስራ ላይ መዋሉን መከታተልና መቆጣጠር፤ ማሰራጨት፣መከታተልና መቆጣጠር፤ እንዲሁም ዓላማውን ለመፈጸም የሚረዱ ሌሎች ሥራዎችን ለማከናወን እንዲያስችለው ዘርፉ በአራት ዳይሬክቶሬት የተከፋፈሎ ተግባራትን ይመራል፡፡ የዳይሬክቶሬቶቹ ኃላፊነትና ተግባራት ከዚህ በታች በዝርዝር ቀርቧል፡: