• +251462204629
  • Hawassa , Ethiopia

ለኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት በ7 ቀን ብቻ ከ153 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡ ተገለጸ፤

ይህ የተገለፀው የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ ድጋፍ አሰባሰቡን በተመለከተ በፅሕፈት ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡ አቶ ተፈሪ አባተ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ይህንን አንድ ምዕራፍ የተሻገረ የህዝባችንን ድጋፍ በሚመለከት ጋዜጣዊ መግለጫ የጠራነው እጅግ በጣም ባጠረ ቀን ውስጥ ህዝባችን ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት ያደረገውን ድጋፍ እውቅና ለመስጠት ነው፤ ያሉ ሲሆን ከዚህ አንፃር ፅንፈኛው የህወሃት ዘራፊ ቡድን መከላከያ ሰራዊታችን ላይ የፈፀመውን ክህደት በመቃወም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ከመከላከያ ሰራዊታችን ጎን በመሆን ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመተማመን ነው ብለዋል፡፡ አቶ ተፈሪ አያይዘዉም በአሁኑ ሰዓት ለመከላከያ ሰራዊታችን ገቢ ማሰባሰብ በጀመርንበት በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ብር 154760405.80 /አንድ መቶ ሀምሳ አራት ሚሊዮን ሰባት መቶ ስድሳ ሺህ አራት መቶ አምስት ብር ከ80 ሳንቲም ወደ ክልሉ የመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ማሰባሰብ አካውንት ውስጥ ገቢ ተደርጓል፡፡ ከዚህ አጠቃላይ ገንዘብ ውስጥ ብር 102,888,435.80 /አንድ መቶ ሁለት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሰማንያ ስምንት ሺህ አራት መቶ ሰላሳ አምስት/ ገቢ የተደረገው በጥሬ ገንዘብ ሲሆን ቀሪው 51,871,970 /ሃምሳ አንድ ሚሊዮን ስምንት መቶ ሰባ አንድ ሺህ ሰጠኝ መቶ ሰባ ብር/ ደግሞ በዓይነት የተሰበሰበ መሆኑን ገልፀው የክልሉ ህብረተሰብ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል በማሳሰብና በድጋፉም ለተሳተፈው ህብረተሰብ ምስጋና አቅርዋለል፡፡

0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *