የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል መንግስት ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ
የአቶ ተፈሪ አባተ መልዕክት
እንኳን ወደ ደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል መንግስት ፋይናንስ ቢሮ ድረገፅ በሰላም መጣችሁ፡፡
ቢሮው የክልሉን የፊስካል ፖሊሲ አተገባበር ማዕቀፍ ማዘጋጀትና መተግብር፣ የክልሉን መንግስት በጀት ማዘጋጀትና ማስተዳደር፣ በተፈቀደው በጀት መሠረት ክፍያ መፈጸም፣ የበጀቱን አፈጻጸም መከታተል፤ የክልሉ መንግስት የበጀት፣ የሂሳብ፣ የክፍያና ጥሬ ገንዘብ እና የውስጥ ኦዲት ሥርዓት መዘርጋትና በስራ ላይ እንዲውል ማድረግ፣ የክልሉን መንግስት የገንዘብ ሰነዶች፣ ገንዘብና ንብረቶች መያዝና ማስተዳደር፣የክልሉ መንግስት የብድርና እርዳታ ስምምነቶችን መፈራረምና ከአጋር ድርጅቶች የሚገኘውን ሀብት ውጤታማና በተቀላጠፈ አኳኋን ማስተዳደርና አፈጻጸሙን መከታተል፣ የክልሉን መንግስት የፋይናንስና ንብረት ኢንስፔክሽን ማከናወን፣ ዘመናዊ የበጀት አስተዳደር፤ የሂሳብ አያያዝ፣ የግዥና የንብረት አስተዳደር፣ በኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት ዘርፍ የተሰማሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ማስተባበርና መቆጣጠር፤ ለሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች የቅድመ ስምሪት የስራ ውል ፈቃድ መስጠት፣ አተገባበራቸውንም በመስክ የመከታታልና የመገምገም እንዲሁም የሀብት ፍሰትና ስርጭት ፍትሃዊነት እንዲረጋገጥ ማስቻል፣ በክልሉ የሚገኙ የመንግስት ልማት ድርጅቶችን እንቅስቃሴ ትርፋማነታቸውንና የገበያ ትስስራቸውን መከታተል፣ መቆጣጠርና አፈጻጸሞችንም በመገምገም ግብረ-መልስ መስጠትና ማስተካከያዎችን ማድረግ፣ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣንና ተግባር መሠረት በበላይነት የመምራት ዋና ኃላፊነት አለበት፡፡Read More